edu 5

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 በካራ ቆሬ አፀደ ህፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2012 ዓ.ም የስራ ዘመን የቢሮ መገልገያዎችና የተለያዩ እቃዎችን ማለትም
- ሎት 1. ቋሚ እቃ ኤሌክትሮኒክስ (6313) የጨረታ ማስከበሪያ 1000
- ሎት 2. የደንብ ልብሶች (6211) የጨረታ ማስከበሪያ 1000
- ሎት 3. የጽህፈት መሳሪያና ሌሎች (6212) የጨረታ ማስከበሪያ 1200
- ሎት 4. አላቂ የትምህርት እቃዎች (6215) የጨረታ ማስከበሪያ 1200
- ሎት 5.የተለያዩ መሣሪያዎች እና መፃህፍት (6219) የጨረታ ማስከበሪያ 500
- ሎት 6. ሌሎች አላቂ እቃዎች (የፅዳት እቃዎች (6218) የጨረታ ማስከበሪያ 4000
- ሎት 7. ቋሚ እቃዎች (6314) የጨረታ ማስከበሪያ 1000 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- የጨረታው ቁጥር 005/2012 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር/supplier list/ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ በባለስልጣኑ በመንግስት አካል የተሰጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፍኬት እና የታክስ ከፋይነት ቲን ቁጥር ሊኖራቸው ይገባል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 ( አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በኮ/ቀ/ክ/ክ ወረዳ 03 በካራ ቆሬ አፀደ ህፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ግራር ባጃጅ መያዣ ከፍ ብሎ ኮንዶሚኒየም አለፍ እንዳሉ ከመስቀሉ ፊት ለፊት በሚገኘው በካራ ቆሬ አፀደ ህፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ክ/ሂ አስተዳደር ቢሮ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ( አስር) ቀናት እሁድና ቅዳሜን ጨምሮ ከጠዋቱ 2፡30-11፡30 ከምሳ ሰዓት ውጪ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ያለውን እቃ ናሙና ወይም ሳንፕል ማቅረብ ግዴታ መሆኑን እየገለጽን በአካል ማቅረብ የማይቻል ከሆነ በፎቶ ወይም ድርጅቱ ድረስ በመውሰድ ማሳየት ግዴታ አለባቸው ።
- አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ሌላው ተንተርሶ መስጠት አይችልም።
- ገዥው በኣካል የሚገዛውን እቃ እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
- ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን (ፋይናንሻል) እና ፎቶ ኮፒውን (ቴክኒካል) ሰነዶችን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ወይም ቢሮ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማንኛውም ቀናት እስከ 11፡30 ሰአት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ።
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ ከረፋዱ 4 ፡30 ይከፈታል።
- የሚቀርበው የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ የድርጅቱ ሀላፊ ስምና ፊርማ የድርጅቱ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር መኖር አለበት።
- ለአሸናፊ ተጫራቾች በሰነዱ ውስጥ የተመለከተውን ጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም እስከ 7 ቀን ድረስ ቀርበው የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን የእቃ ዋጋ 10% ገቢ አድርገው ውል መዋዋል አለባቸው::
- መስሪያ ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ 6ወር ድረስ ውሉን ቢያድስም ባያድስም የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታ ሰነድ ላይ ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዮች ካሉ የማብራሪያ ጥያቄ በፅሁፍ ከጨረታው መክፈቻ 2 ወይም 3 ቀን በፊት ማቅረብ ይቻላል።
- ተጫራቾች በጨረታው ሂደት ቅሬታ ካላቸው በት/ቤቱ ክ/ሂ/ግ/ን/ አስተዳደር እና ጠ/አገ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቅሬታቸውን በጽሁፍ ማቅረብ ይችላሉ። በደጋፊ የስራ ሂደቱ የማይፈታ ከሆነ ደረጃውን ጠብቀው ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ይችላሉ። የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ5 ቀን (አምስት) ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ያላቀረበ ተጫራች በውጤቱ እንደተስማማ ተቆጥሮ ግዥው ከአሸናፊው ጋር ውል ይፈጽማል።
- አሸናፊው ድርጅት የግዢውን ውል ከፈረመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ እቃውን ገቢ ማድረግ አለበት።
- የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክር ማንኛውም ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች ለሚያስገባቸው ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት እንዲሁም ያሸነፉበትን እቃዎች ት/ቤቱ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው ።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
አድራሻ፡- ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ካራ ቆሬ ግራር ኮንደሚንየም መስቀሉ ጋር ከወረዳ 03 ጤና ጣቢያ ወረድ ብሎ ይገኛል ።
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር 011 348-19 99/
011-832-74 28
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 በካራ ቆሬ
አፀደ ህፃናት አና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት
___________________________________________________________________________________
Category : Cleaning and Janitorial., Cleaning and Janitorial Equipments, Education and Training., Books and Education Materials, Office Supplies and Stationery, Office Items and Equipment, Stationery Supplies, Purchase., Textile and Leather Products, Textiles/ Fabrics and Wearing
Posted Date :አዲስ ዘመን ረቡዕ መጋቢት 9 ቀን 2012
Deadline : 2020-03-28