consul arada2

consul arada2


ለኮንስትራክሽን ሥራዎች ስምክር/ ኮንሰልታንሲ

ሥራ ቅጥር የወጣ የጨረታ ማ ስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 10/2012

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአራዳ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች ለሚያሠራቸው የግንባታ ሥራዎች አማካሪዎችን በጨረታ በማሳተፍ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን አቅርበው የተሟላ የሰው ኃይል ያላቸው በተጠቀሰው የካሌንደር ቀን ውስጥ ሥራው እንዲጠናቀቅ ማማከር የሚችሉ በተጨማሪም የሚቀጥሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን አንድ ሎት ብቻ መውሰድ ይችላሉ፡፡

በመሆኑም ለሥራው ፍላጎት ያላቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

ለሥራ ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር (የ2012 ዓም) የከፈሉ፣ ለ2012 የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚ/ር ለማማከር ሥራ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ዋናዉንና የማይመለስ ኮፒ በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መዉሰድ ይችላሉ፡፡
በጨረታው የሚወዳደሩ ድርጅቶች በአዲስ አበባ ኮንስትራከሽን ቢሮ አጭር ምዝገባ /short registration / ያካሄዱ መሆን አለባቸው፡፡
የሚሳተፉት ድርጅቶች ከላይ ከተጠቀሰው ሎት ማማከር ሥራ ከደረጃ 5 ( category 5) እና ከዚያ በላይ ያላቸው፡፡ በሚመለከታቸው ብቻ መሳተፍ ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ አስረኛው የሥራ ቀን አራዳ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት 3ተኛ ፎቅ ላይ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናውና (Original) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ) ብር ብቻ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡

ተጫራቾች አንድ ዋና(Original) እና ሁለት ቅጂ(copy) የፋይናንሽያል ጨረታ ሰነድ በተለያየ ኤንቬሎፕ በማዘጋጀትና በሰም በማሸግ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት 3ተኛ ፎቅ ላይ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ጨረታው የሁለት ደረጃ ጨረታ ሲሆን፤ ቴክኒካል ከ80% ፋይናንሻል ከ20% በመያዝ በድምሩ ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገበ ብቻ የሚያልፍ ይሆናል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND or BID SECURITY) የጨረታ ዋጋ(ብር) 5,000.00 ( አምስት ሺ ብር ብቻ) በባንክ ትዕዛዝ (CPO) ወይም UNCONDITIONAL BANK GUARANTEE በአራዳ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድን በጨረታው ሰነድ መሰረት የመጫረቻ ሰነድ በማዘጋጀት ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ለየብቻ አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ፊርማ እና ማህተም በማድረግ በአስራ አንደኛው(11) የሥራ ቀን ከጠዋቱ ሁለት ተኩል (2 ፡30) እስከ አራት ሰዓት (4 ፡00) ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ በአራዳ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ ቤት 3 ተኛ ፎቅ ላይ በመቅረብ በሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በአስራ አንደኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ አራት ሰዓት ተኩል (4 ፡30) ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
አማካሪው ድርጅት ዲዛይን የማስተካከል ሥራ ፤የግንባታ ክትትል፣ ውል የማስተዳደር ሥራ እና በባለቤት እውቅና እና ፍቃድ የዲዛይን ማሻሻያ ይሠራል፡፡

ተጫራቾች በጊዜያዊነት የሚያቀርቧቸው ባለሞዎች በድርጅታቸው ውስጥ ብቻ የሚሠሩ ወይም ለድርጅቱ ብቻ የፈረሙ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ በድርጅቱ ኃላፊ ወይም ተመሳሳይ ተግባር እና ስልጣን በተሰጠው አካል እና በተቀጣሪው(በፈራሚው) ባለሙያ የተፈረመ ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ አንድ ባለሙያ ከሁለት እና ከዚያ በላይ ፈርሞ ከተገኘ ድርጅቶቹ በጨረታው የተሳተፉም ሆነ ያልተሳተፉ ሁሉም ድርጅቶች ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናል፡፡

በተጨማሪም የትኛውንም ከላይ የተዘረዘሩትን ሆነ በጨረታው ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ህጎች አለማክበር፣ በሚያስገቡት የመጫረቻ ሰነዶቻቸው በሁሉም ገፆች ላይ ማህተም እና ፊርማ አለማድረግ እና ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአራዳ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ ቤት


Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 21 ቀን 2012

Deadline: June 11, 2020


© walia tender

Report Page