construct 3

የማሽነሪዎች ኪራይ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በከምባታ ጠምባሮ ዞን የአንጋጫ ወረዳ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ ቤት በህብረተሰብ ተሳትፎ በ2012 በጀት ዓመት በአንጋጫ ከተማ የውስጥ ለውስጥ ለሚሰራ መንገድ ጥገናና እድሳት ለማስደረግ ግሬደር እና ኡሩሎ በሰዓት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስስዚህ ተጫራቶች፡
በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስና ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000/ ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
በዘርፉ የተዘገጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በመንግስት የስራ ሰዓት ብቻ በመቅረብ በኢትዮ ብር 50/ ሃምሳ ብር/ ብቻ ሰነዱን በመግዛት በመ/ ቤታችን ቢሮ ቁጥር 2 በሚኖረው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው በ16 ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ በ8 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ8 ፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
አሸናፊው ድርጅት ወይም ድርጅቶች አሸናፊነታቸው በተገለጸ በ10 ቀናት ውስጥ ውል ይፈርማሉ፡፡ ከአሸናፊ ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ያስይዛሉ፡፡
ተጫራቾች የአንዱን ዋጋ ከነቫቱ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተበቀ ነው፡፡
በደ/ ብ/ ብ/ ሕ/ ክ/ ም/ በከምባታ ጠምባሮ ዞን የአንጋጫ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ ቤት ( አንጋጫ)
_______________________________
Category : Construction and Construction Machinery, Construction Machinery and Equipment, Machinery., Machinery Rent, Rent.
Posted Date : አዲስ ዘመን አርብ መጋቢት 11 ቀን 2012
Deadline :2020-04-04[መጋቢት 26]