con yagnangatom menhar1

con yagnangatom menhar1


የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ በደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር የኛንጋቶም ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት በመደበኛ ካፒታል በጀት በካንጋቴን ከተማ የመናኸሪያ ግንባታን በግንባታ መስክ የተሰማሩ ሕጋዊ ተጫራቾችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት

ደረጃ ሰባት እና ከዚያ በላይ ጠቅላላ ወይም ሕንፃ ሥራ ተቋራጭ የሆነ፤

በኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ወይም በክልሉ ተመዝግቦ ለ 2012 ዓ.ም የበጀት ዓመት ከላይ በተራ ቁጥር አንድ በተጠቀሰው ደረጃ መሠረት በዘርፉ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ያለው፣
ለ2012 ዓ.ም የበጀት ዓመት በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፤
የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፤
የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፣
የግብር ግዴታን በመወጣት ሥልጣን ካለው አካል ወይም ገቢዎች ባለሥልጣን ለስጀት ዓመቱ በጨረታ መሳተፍ የሚያስችለውን የታደሰ የታከስ ክሊራንስ ሠርተፍኬት የያዘ Mald tax clearance certificate/
በፌዴራል ወይም በክልሉ የግዢ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሥልጣን ከተሰጠው የሚመለከተው አካል በዘርፉ በአቅራቢነት በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ / Registered in FPPA or PPA Suppliers List /
ከዚህ ቀደም የወሰዳቸውን የግንባታ ሥራዎች፡- በጥራትና በወቅቱ ገንብቶ የሚያስረክብ ለመሆኑ፤ የግንባታ ጥራት ማጓደል ፤ማዘግየት እና ውል ማቋረጥ ችግር የሌለበት ለመሆኑ ሥልጣን ከተሰጠው መ/ቤት ማስረጃ ያለው፤ ከዚህ ቀደም የግንባታ ፕሮጀክት ወስዶ በግንባታው ወይም በፕሮጀክቱ የውል ስፔስፍኬሽን እና ማጠናቀቂያ ቀናት በሚፈለገው ጥራትና የማጠናቀቂያ ቀናት በማጠናቀቅ ለአሰሪው ባለ በጀት መ/ቤት በወቅቱ ያላስረከበ፤ ውል ያቋረጠ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡ ለዚህም ማስረጃ ከቀረበ ከጨረታው ውድድር በቀጥታ ውጪ ይደረጋል ወይም ይሰረዛል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ለመግዛት ሲቀርቡ ይህን ማስረጃ ካላቀረቡ የጨረታ ሰነዱን መግዛት አይችሉም፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን ይህ ጨረታ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከኛንጋቶም ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዢ እና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ክፍል የማይመለስ ብር 300 ( ሦስት መቶ) በመክፈል የጨረታ ሠነዱን በመውሰድ በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡
ተጫራቾች በጨረታ መሳተፍ የሚያስችላቸውን የጨረታ ማስከበ ሪያ 15,000.00 ( አስራ አምስት ሺህ) ብር ከታ ወቀ ባንክ በሲፒኦ ብቻ በማዘጋጀት ለብቻው በአንድ ፖስታ በማሸግ ከጨረታው ቴክኒካል ኦርጂናል ዶክመንት ጋር በማስገባት ማስያዝ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች የተገዛውን የጨረታ ሠነድ በመሙላት እና በማዘጋጀት አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን አቀራረቡም ቴከኒካል እና ፋይናንሻል በተለያየ ፖስታ ተሞልቶ እና ተዘጋጅቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ /ቴክኒካሉ ላይ ቴከኒካል ኦርጂናል እና ቴክኒካል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ እንዲሁም ፋይናንሻሉ ላይ ፋይናንሻል ኦርጂናል እና ፋይናንሻል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በሃያ ሁለተኛው (22 ኛው) ቀን ( የሥራ ቀን) ከሆነ ብቻ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከ 3 ፡00 ሰዓት እስከ 6 ፡25 ሰዓት ድረስ መግባት ይኖርበታል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት 6.30 ሰዓት ታሽጎ ከሰዓት በኋላ 8 ፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው አከፋፈት ሥነሥርዓትም በሁለት መንገድ ሆኖ ቴከኒካሉ በመጀመሪያ ደረጃ ተከፍቶ ከተገመገመ በኋላ ፋይናንሽያል ዶከመንት ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0983974525 ወይም O989116717 በመደወል መረዳት ይችላሉ፡፡

በደ/ ብ/ ብ/ ህ/ ክ/ መ በደቡብ

ኦሞ ዞን አስተዳደር ያኛንጋቶም

ወረዳ ፋ/ ኢ/ ል/ ጽ/ ቤት

ካንጋቲን



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 27 ቀን 2012

Deadline: June 25, 2020


© walia tender

Report Page