con wolkitie3 kera

con wolkitie3 kera

Walia Tender

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዢ መለያ ቁጥር-012/2012

በደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ ፋ/ኢ/ል ጽ/ቤት ለወልቂጤ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የሚውል ማለትም፡- የዘመናዊ ቄራ ግንባታ ግዢ ለመፈጸም በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ባላቸው ተቋራጮች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት፡- ከዚህ በታች የተገለጹት መስፈርቶች የሚያሟሉ ተቋራጮች በጨረታው እንዲሳተ ተጋብዘዋል፡፡

የዘመኑ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ፡፡
ህጋዊና የታደሰ የስራ ፍቃድ ኦርጅናል አና ኮፒ ማቅረብ የሚችልና የዘመኑ የስራ ግብር የከፈሉ፣ቲን ነምበር ተመዝጋቢ የሆነ እና ማቅረብ የሚችል፡፡
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን፤ በ 22 ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡ 00 ሰዓት ታሽጎ በዛው አለት ከጠዋቱ 4 ፡ 30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቴክኒካል ዶክመንት ይከፈታል፡፡

ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር ብቻ / አዲስ ክ/ከተማ ከሚገኘው የገቢዎች ቅርንጫፍ ቢሮ በመክፈልና ሪሲቱን በመያዝ ከወልቂጤ ከተማ ፋ/ኢ/ል/ፅ/ቤት ግዥ ክፍል ዘወትር በስራ ሰዓት በመውሰድ የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ዶክመንት ሲያቀርቡ ከስር በተገለጸው መሰረት ይሆናል ሀ/ለቴክኒካል ዶክመንት 1 ኦርጅናልና 2 ፎቶ ኮፒ ለየብቻቸው በማሸግ የጨረታ ማስከበርያ የ 100,000.00/ አንድ መቶ ሺህ ብር / በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ . (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከቴክኒካል ኦርጅናል ጋር በማድረግ በእናት ፖስታ አድርጎ በሰም በማሸግ ቴክኒካል በሚል በመለያት እና ለፋይናንሽያል ዶክመመንት 1 ኦርጅናልና 2 ፎቶ ኮፒ ለየያብቻቸው በማሸግ በእናት ፖስታ አደርጎ በሰም በማሸግ ፋይናንሽያል በሚል በመለየት አስከ 22 ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡ 00 ሰዓት ድረስ ብቻ ወልቂጤ ከተማ ፋ/ኢ/ል/ ፅ/ቤት-ግ/ን/አስ/ዋና/የስራ/ሂደት ክፍል ውስጥ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን የሚገባ ሲሆን የቴክኒካል ዶክመንት ጨረታው 4 ፡ 30 ሰዓት ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቻ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ከቴክኒካል ግምገማ ወደ ፋይናንሽያል ያለፉ ተወዳዳሪዎች ፋይናንሽያል ዶክመንት የሚከፈትበት ቀነ ቀጠሮ ተቋሙ በማስታወቂያ የሚገልጽ ይሆናል፡፡
በBC(ቢሲ) /GC (ጂሲ) ደረጃ 5 እና ከዚህ በላይ ፈቃድ ያለው/ያላት ብቻ መወዳደር የሚችሉ መሆኑ፡፡
በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁተወካዮች ከሆኑ ህጋዊ ውክልና ይዞይዛ መቅረብ አለባቸው፡፡
ተወዳዳሪዎች ሰነድ ለመግዛት ሲቀርቡ ከጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ልማት መምርያ የድጋፍደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጫራቾች በፌዴራል ወይም በክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ወይም በዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ መምሪያ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው የእውቅና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡

ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታው ኮሚቴ ጨረታውን ሊከፍት ይችላል፡፡
በአፈጻጸም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መወዳደር አይችሉም።
የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይዘዋወራል፡፡
ተጫራቾች በመወዳደርያ ሰነዳቸው በሁሉም ገጽ እና ፖስታ ላይ ስማቸው፣ ፊርማቸውና ማህተም ማሳረፍ አለባቸው፡፡
በጨረታው ሂደት ውስጥ ለየትኛውም ግምገማ ተሻሽሎ የወጣው የክልል ግዢ መመርያ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን አንገልጻለን፡፡

ለበለጠ መረጃ አድራሻ:- በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ብሩክ ህንጻ ፊት ለፊት ቴሌ አጠገብ ከተሰራው አዲሱ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ህንጻ ውስጥ ኛ ፎቅ ወደ ቀኝ ሲታጠፉ የወ/ከ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም

በስልክ ቁጥር  0113301548/ 0113302547 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡

በደቡብ ብ/ ብ/ ህ/ ክ/ መንግስት በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ ፋ/ ኢ/ ል ጽ/ ቤት


Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 26 ቀን 2012

Deadline: June 24, 2020


© walia tender

Report Page