con road side market 12

con road side market 12


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ግዥ ፈጻሚው መ/ቤት፡- ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ

የጨረታ ቁጥር፡ ATA-NCB-W-2020-0008

የጨረታው ርዕስ/ስያሜ የመንገድ ዳር የገበያ ማዕከል /Roadside Market Shade/ ግንባታ ሥራ

ግንባታው የሚካሄድበት አካባቢ በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ ሞሮኮ ሾንዶሎ ቀበሌ እና ጋሞ ዞን ምዕራብ አባያ ወረዳ አንኮበር ቀበሌ

የግንባታ ስራዎቹ በሁለት ሎት የተከፈሉ ሲሆን ከዚህ እንደሚከተለው በዝርዝር ቀርቧል።

ተጫራቾች በመረጡት አንድ ሳይት/ሎት ብቻ መሳተፍ ወይም መወዳደር አለባቸው።
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
i. ተጫራቾች በጨረታ ለመወዳደር በዚሁ የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ሆኖ ህጋዊ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
ii. የግንባታ ሥራ ብቃት የሚያረጋግጥ ከደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ ማቅረብ የሚችሉ።
iii. በግንባታ ዘርፍ ስራ ላይ ላለፉት አምስት ዓመታት ቢያንስ ሶስት የግንባታ ስራዎችን በአመርቂ ሁኔታ ሰርቶ ያስረከበ ለዚህም ማረጋገጫ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
iV. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ
V የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ወይም በግዥ ኤጀንሲ ዌብ ሳይት ላይ የተመዘገቡ
Vi. የግብር ግዴታቸውን ስለመወጣታቸው የሚያሳይ ማረጋገጫ የሚያቀርቡ

8. ተወዳዳሪዎች ሰነዳቸውን ሲያቀርቡ የፋይናንስና የቴክኒክ ሰነዶችን ለይተው በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

9.ተወዳዳሪዎች ለስራው የሚያቀርቡትን ዋጋ መሥሪያ ቤቱ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ባቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የተሞላ ዋጋ መቅረብ አለበት፣

10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 / ሃምሳ ሺ/ በ ባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ወይም የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው። የባንክ ዋስትና የሚያሲዙ ከሆነ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የ118 ቀን የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የኢንሹራንስ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

11. ጨረታው ሰኔ 8 ቀን 2012 ዓ. ም ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4 ፡30 ሰዓት ላይ የተጫራቶች የቴክኒክ እና የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ዋና መስሪያ ቤት አዲስ አበባ በኦፕሬሽን ዳይሬክተር በሚገኝበት ህንፃ 7 ኛ ፎቅ ( ስተርሊንግ ህንፃ) በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል

12. በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዚህ በታች በተገለጸው የኢሜል አድራሻ አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ።

13 ተጫራቶች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማብራሪያ ቢፈልጉ ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ መጠየቅ ይችላሉ።

14 መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ ማብራሪያ አድራሻ

1. የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ

ስልክ ቁጥር +251-115-570678/85 ወይም +2519-646029, ፋክስ + 251-115 570668

ኢሜል /E-mail: Yohannes.Tadesse@ata.gov.et or Melaku. Getahun@ata.gov.et

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

2. በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ሮሪ ሆቴል ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር፡ 0462127582 ወይም +251916825941


የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ  ሃዋሳ ኢትዮጵያ



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 20 ቀን 2012
Deadline: June 15, 2020


© walia tender

Report Page