con ethi biodiversit2

con ethi biodiversit2

Walia Tender

የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት ግንባታው ያልተጠናቀቀ የፍቼ ጂን ባንክ ከነእቃው ለማስገንባት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ጋብዞ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም:

የደረጃ 4 እና በላይ የግንባታ ፈቃድ ያላችሁ፣
የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፣
ህጋዊ የዘመኑ የታደሰ የሥራ ፈቃድ ያለው፣
የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
የገቢዎች የመጫረት መብት ፈቃድ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፣
በመንግስት የግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ምዝገባ ማስረጃ የሚያቀርብ፣

የመልካም ስራ አፈፃፀም ሊያቀርብ የሚችል፣ (ከ3 ዓመት ወደዚህ ያለ ቢያቀርብ ይመረጣል)
ተጫራቹ የሚያቀርበው ዋጋ ቫትን የሚያካትት ለመሆኑ በሰነዱ ላይ በግልጽ ማመልከት ይኖርበታል፡፡

ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ብር 100 ( አንድ መቶ) በመክፈል ከኢንስቲትዩቱ ቢሮ ቁጥር 13 መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 ( ሁለት መቶ ሺህ ብር ) በባንክ በተረጋገጠ ቦንድ ፣ ቼክ (CPO) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር የግድ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸሁን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል ሰነድ፦ ኦርጅናልና ኮፒ፣ፋይናንሻያል ሰነድ : ኦርጅናልና ኮፒ ለይቶ በማሸግ እንደገና ደግሞ ቴክኒካሉን ብቻውን ፋይናንሻያሉን ብቻውን አሽጋችሁ በሰነዱ ላይ ስም፣ ሙሉ አድራሻ፣ ፊርማችሁንና ህጋዊ ማህተማችሁን ማስቀመጥ አለባችሁ፡፡

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በወጣ ተከታታይ በ21 ኛው ቀን ከሰዓት 8 ፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን 9 ፡00 ሰዓት በኢንስቲትዩቱ ግዥ ክፍል ( አዳራሽ ) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል :: ሆኖም ግን የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡


ኢንስቲትዩቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡


አድራሻ፡- የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ኬኒያ ኤምባሲ ጎን ነው፡፡

ተጨማሪ ማስረጃ ቢፈልጉ በስልክ ቁጥር 011-661-66-43 /011-661-53-69 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡


የኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 25 ቀን 2012

Deadline: June 20, 2020


© walia tender

Report Page