con eng 15

con eng 15


መልካም የላብ አደሮች ቀን

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዚ መለያ ቁጥር-009/2012

በደቡብ ብብህ/ክ/መንግስት በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ ፋ/ኢ/ል ጽ/ቤት ለወልቂጤ ከተማ እስተዳደር አገልግሎት የሚውል ማለትም፡-

የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ዳር መብራት ዝርጋታ ግዢ ለመፈፀም በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ባላቸው ተቋራጮች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-

ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተቋራጮች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡

1ኛ/ በዘመኑ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ፡፡
2ኛ/ ህጋዊና የታደሰ የስራ ፍቃድ ኦርጅናል ማቅረብ የሚችልና የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉ፣ ቲን ነምበር ተመዝጋቢ የሆነ እና ማቅረብ የሚችል፡፡
3ኛ/ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 21 ቀናት እየር ላይ የሚቆይ ሲሆን፤ በ22ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቴክኒካል ዶክመንት ይከፈታል፡፡
4ኛ/ ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር ብቻ እዲስ ከከተማ ከሚገኘው የቢዎች ቅርንጫፍ ቢሮ በመክፈልና ሪሲቱን በመያዝ ከወልቂጤ ከተማ ፋ/ኢ/ል ፅ/ቤት ግዥ ክፍል ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
5ኛ ተጫራቾች የጨረታ ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ዶከመንት ሲያቀርቡ ከስር በተገለጸው መሰረት ይሆናል።
ሀ/ ለቴክኒካል ዶከመንት አርጅናልና 2 ፎቶ ኮፒ ለየብቻቸው በማሸግ የ100,000.00/አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከቴክኒካል ኦርጅናል ጋር በማድረግ በእናት ፖስታ እድርጎ በሰም በማሸግ ቴከኒካል በሚል በመለየት እና ለፋይናንሽያል ዶክመንት ኦርጅናልና 2 ፎቶ ኮፒ ለየብቻቸው በማሸግ በእናት ፖስታ አድርጎ በሰም በማሸ ፋይናንሽያል በሚል በመለየት እስከ በ22ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ወልቂጤ ከተማ ፋ/ኢ/ል ፅ/ቤት-ግ/ን/አስ/ዋና/ስራ/ ሂደት ክፍል ውስጥ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን የሚገባ ሲሆን የቴክኒካል ዶከመንት ጨረታው 4፡30 ሰዓት ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
6ኛ/ ከቴክኒካል ግምገማ ወደ ፋይናንሽያል ያለፉ ተወዳዳሪዎች ፋይናንሽያል ዶከመንት የሚከፈትበት ቀን ቀጠሮ ተቋሙ በማስታወቂያ ሚገልጽ ይሆናል፡፡
7/ በኤሌክትሮ መካኒካል ደረጃ 3 እና ከዚህ በላይ ፈቃድ ያለው/ ያላት ብቻ መወዳደር የሚችል መሆኑ፡፡
8ኛ/ በጨረታው ለመወዳደር ሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ህጋዊ ውክልና ይዞ/ይዛ መቅረብ አለባቸው፡፡
9ኛ/ ተወዳዳሪዎች ሰነድ ለመግዛት ሲቀርቡ ከጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ልማት መምሪያ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
10ኛ/ መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኝ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡-

1/ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታው ኮሚቴ ጨረታው ሊከፍት ይችላል፡፡
2/ መ/ቤቱ ከሸጠው ሰነድ ውጭ በሌላ ሰነድ ሞልቶ መወዳደር አይቻልም፡፡
3/ የጨረታው መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይዘዋወራል፡፡
4/ ተጫራቾች በመወዳደርያ ሰነዳቸው በሁሉም ገጽ እናት ፖስታ ላይ ስማቸው ፣ ፊርማቸውና ማህተም ማሳረፍ አለባቸው፡፡
5/ በጨረታው ሂደት ውስጥ ለየትኛውም ግምገማ ተሻሽሎ የወጣው የክልሉ ግዢ መመርያ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑ እንገልፃለን፡፡


ለበለጠ መረጃ ስድራሻ፡- በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ብሩክ ህንጻ ፊት ለፊት ቴሌ አጠገብ ከተሰራው አዲሱ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ህንጻ ውስጥ 1ኛ ፎቅ ወደ ቀኝ ሲታጠፉ የወ/ከ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011 330 51 48/011 330 25 47 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡

በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት

በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ

ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት


Posted:አዲስ ዘመን ሚያዝያ 22 ፥2012

Deadline: May 21, 2020




© walia tender®

Report Page