con AA TEACHERS ASSOS1
Walia Tender ADMIN1 TAD![](/file/30597a0a9a32f84e4007f.jpg)
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ልዩ ቦታው አቧሬ ወደ ቤልኤር ሆቴል በሚወስደው መንገድ ከጄነራል ሞተርስ አለፍ ብሎ ዋናው መንገድ ላይ 2B+G+6 ሆስፒታል እና 2B+G+9 ሁለገብ ሕንፃ ግንባታዎችን ለማሰራት የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት አቅዷል፡፡
ስለሆነም በመጀመሪያው phase ለሚያሰራው 2B+G+9 ሁለገብ ሕንፃ ለማሰራት ስለሚፈልግ ተጫራቾች ለሥራው ሕጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የበጀት ዓመቱን ግብር የከፈሉ፣ የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምስክር ወረቀት እንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ BC-1andGC-1 የሆኑ የሥራተቋራጮች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታሰነዱንቄራቡልጋሪያ መስቀለኛ መንገዱን ወረድ ብሎ በሚገኘው ኖክ (NOC) ማደያ ፊትለፊት ባለው ብርሃን መካከለኛ ክሊኒክ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን ጨረታው በዚሁ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 25 ተከታታይ ቀናት ድረስ የማይመለስ 500 ብር ( አምስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን፤
ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በመሙላትና በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ (envelope) በማዘጋጀት የጨረታ መመሪያ በሚያዘው መሠረት ከላይ በተጠቀሰው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ዋና ጽ/ ቤት በተዘጋጀው የሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በጋዜጣው ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስ ከ 26 ኛው ቀን ከ ረፋዱ 4፡30 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን (Technical & Financial Proposals) ለእያንዳንዱ አንድ ኦሪጂናልና ሁለት ኮፒ ማገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የቅድመ ብቃት ደረጃ ጨረታ ሰነድ (Original Technical & Financial Proposals) በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4 ፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከ 15 ደቂቃ በኋላ ከረፋዱ 4 ፡45 ሰዓት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት Original Technical & Financial Proposal ይከፈታል፡፡
ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ጽ/ ቤት
Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 25 ቀን 2012
Deadline: June 25, 2020
© walia tender