con የምስ/ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ደ/ማርቆስ

con የምስ/ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ደ/ማርቆስ

ADMIN1 TADELE

ለ 2 ኛ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የምስ/ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት በደ/ማርቆስ ከተማ እያስገነባው ላለው

2B+, G+6 ቢሮና ሁለገብ አዳራሽ ግንባታ፣
የግንባታ ግብዓቶች ማለትም አልሙኒያም ሥራዎች

(የፀሐይ መከላከያ (Sun Breaker)፣
የደረጃ መደገፊያ (Hand rail)፣
ከመስታወትና አልሙኒየም የሚሰራ ብርሃን አሳላፊ ጣራ (sky light)
ልዩ ልዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣
የሳኒተሪ ዕቃዎች፣
ሊፍት (አሳንሰር)፣
ጀኔሬተር፣
የፍሳሽ መከላከያ (Damp Proofing and water proofing)

እና የመሳሰሉትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

በመሆኑም ከሁሉም ሥራዎችና ግብዓቶች

በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው::
የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
ተጫራቾች የተዘረዘሩትን መረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
ተጫራቾች ኣንዱን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ ሂሳብ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው በምስ/ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ይሆናል።
ዋጋ የሚሞላው በነፃ ገበያ ላይ በተመሰረተ መሆን ይኖርበታል።
ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን፣የግብዓቱን ወይም የሥራውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ለምስ/ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ተብሎ በማሰራት ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ አለባቸው።
ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ኦርጅናል አንድኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግና ሁለቱንም ፖስታዎች በአንድ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግና ከላይ በሁለቱም ፖስታዎች ላይ የተፃፉትን በሙሉ በማጠቃለያ ፖስታው ላይ በማስፈር መመለስ አለባቸው። ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ በአየር ላይ የሚቆይ ሆና ደ/ማርቆስ ተማ ምስ/ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል።
ጨረታው በ11 ኛው ቀን በ4 ፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4 ፡30 ይከፈታል።

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል።
ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው የሚታሸገውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ የተገለፀውን ሰዓት ጠብቆ ይሆናል።
ተጫራቶች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በተመለከተው መሰረት የእያንዳንዱን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ መግለፅ ኣለባቸው::

ስርዝ ድልዝ ካለ ጨረታው ተቀባይነት አይኖረውም።
በማንኛውም ሁኔታ ተጫራቶች በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ተመስርቶ/ መጫረት አይችሉም።
የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቶች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

ግብዓቶች የሚቀርብበት ቦታ ምስ/ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ደ/ማርቆስ ከተማ መሆን እንገልጻለን።
በጨረታ ማስታወቂያው ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩ በግዥ መመሪያው መሠረት ተገዥ ይሆናሉ።

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ከምስ/ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 05 በግንባር ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 058 771 744 ወይም በሞባይል ቁጥር 0920523318 /091245193 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ የምስ/ ጎጃም ዞን ጽ/ ቤት



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 27 ቀን 2012

Deadline: June 14, 2020


© walia tender

Report Page