com sale amhara design 22

com sale amhara design 22


እስከ ግንቦት 17 አ.ም ብቻ ልዩ ቅናሽ በቤዚክ ሰብስክሪብሽን አድርገናል ለበለጠ መረጃ 0919415260 ይደውሉልን

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ሠነድ ቁጥር፡- አዲቁሥድ -12/2012

አማራ የዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ድርጅት ለጣና በለስ የተቀናጀ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ለግንባታ ክትትልና ኮንትራት አስተዳደር ስራዎች አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተገለፁ ቋሚ እና አላቂ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ::

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርት አሟልቶ በጨረታው መወዳደር ይችላል::

በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምዝገባ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
ተጫራቾች ዋስትና ለሚጠይቁ እቃዎች በሙሉ የዋስትና ሰነድ ማቅረብ ይኖርባችኋል::
ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ባህርዳር ዋ/መ/ቤት ቢቁ 023 በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
ጨረታው ግንቦት 27/2012 ዓ, ም በ8 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8 ፡30 ለመገኘት የቻሉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች የቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ እንዲቀርብ ለሚጠይቁ ግዥዎች ለየብቻ በማድረግ የቴክኒካል ሰነድ እንዲቀርብ ለማይጠይቁ ግዥዎች ደግሞ የፋይናንሻል ሰነድ ብቻ በማዘጋጀትና በጥንቃቄ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በሲፒኦ ወይም እንደተጠየቀ ወዲያውኑ በሚከፈል የባንክ ጋራንቲ በፖስታ አሽገው እስከ ጨረታ መዝጊያው ቀንና ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 023 ማቅረብ ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ::
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ፡ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ፡ስልክ ቁጥር 058-218-02-73 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 058-218-05-50 ወይም 058-218-05-60 በመላክ መጠየቅ ይቻላል፡፡

አማራ የዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ድርጅት

ባህርዳር



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 11 ቀን 2012
Deadline: June 4, 2020


© walia tender

Report Page