cater kilnto ketero maref1

cater kilnto ketero maref1

ADMIN SELAMAWIT

የጨረታ ማስታወቂያ

በቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ለቀጠሮ ለህግ እስረኞች ለምግብ አገልግሎት የሚውሉ በጥሬው

የተከካ አተር ክክ፣ በጥሬው የተከካ ባቄላ ክክ፣ የተቆላ አተር ክክ፣ የተቆላ ባቄላ ክክ፣ ምስር ክክ፣
ጨው፣ ተቀንጥሶ የተዘጋጀ ዛላ በርበሬ፣ ቀይ ሽንኩርት፣ጥሬ ጎመን ዘር፣ የዳቦ እርሾ፣ የዳቦ ማኮፈሻ፣
ካሮት፣ ድንች፣ ጥቅል ጎመን፣ የሻይ ቅመም፣ ቅርንፉድ፣ ጦስኝ፣ ኮረሪማ፣ ጥቁር አዝሙድ፣ ቃሪያ፣
ሻይ ቅጠል፣ነጭ ሽንኩርት፣ ዕርድ፣ ደረቅ ዝንጅብል የተላጠ፣ ነጭ አዝሙድ፣ ጥሬ አብሽ፣ ቲማቲም ድልህ፣
ለጋ የምግብ ቅቤ፣ ክኖር፣ ጥምዝ፣ ከሙን፣ ቆንዶ በርበሬ፣ በሶብላ እና
የባህርዛፍ ማገዶ እንጨት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር በውል ተዋውሎ መግዛት ይፈልጋል::

በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መመሪያና መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው የተገለፀ መሆን አለበት፡፡

የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣የታደሰ የዘመኑን ንግድ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡

የመንግሥት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል አቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የዘመኑን ግብር ከፍለው ስለማጠናቀቃቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም::
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና

ለቀጠሮ ማረ/ቤት አስተዳደር ገንዘቡን ገቢ በማድረግ ከባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ 50,000.00 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡ : እንዲሁም የባንክ ዋስትና የሚያስይዙ ተጫራቾች የቆይታ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 60 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል፡፡

ተጫራቶች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋማቅረቢያዎችን / ፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለበት፡፡ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ በአንድ ላይ አሽጎ ያቀረበ ተወዳዳሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ውጭ ይደረጋል፡፡

ማንኛውም ተጫራቾች የሚያስገቡት ሰነድ ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በሰም በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር የሚጫረትበት በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ እና በሁሉም የመጫረቻ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን ስርዝ ድልዝ፣ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ፣ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዙት ሲፒኦ ከቴክኒክ ሰነዶች ጋር በአንድ ላይ ታሽገው ማቅረብ አለባቸው
ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 / ሃምሣ ብር / የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቀጠሮ ማረፊያ ቤቶች አስተዳደር ስም በአካውንት ቁጥር 1000007971347 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይችላሉ:
ጨረታው በ 2 /10/2012 ዓም ከረፋዱ 5 ፡ 00 ሰዓት ታሽጎ ከረፋዱ 5 ፡ 30 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን በመስሪያ ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡

መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ::

አድራሻ:- ቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር / ቂሊንጦ/

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖስጂ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር -- 011 47163 33/ 0114718986

የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር / ቂሊንጦ/



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 25 ቀን 2012

Deadline: June 9, 2020


© walia tender

Report Page