car rent suger corp178

car rent suger corp178


የጨረታ ማስታወቂያ ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ

የወጣ የጨረታ ቁጥር LP/OT/29/SC/2012

ስኳር ኮርፖሬሽን ለ2012/13 ዓም የሎቤድ ትራንሰፖርት አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

1 በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ የ2012 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የመነግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::

2. ጨረታው ሰኔ 9 ቀን 2012 ዓ. ም. ከቀኑ በ 8 ፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡ ተ ጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በቁጥር 4 ከተገለፀው አድራሻ ሰኔ 9 ቀን 2012 ዓ. ም. ከቀኑ በ 8 ፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 ( ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በተራ ቁ. 4 ከተመለከተው ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡

4. ጨረታው የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ነው፡፡

ስኳር ኮርፖሬሽን

ግዥና ሎጀስቲክስ

ካሳንቺስ፣ ከንግድ ሚኒስቴር በስተቀኝ ገባ ብሎ

ኪያሜድ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ጀርባ ባለው

አዲሱ ሕንፃ 4 ኛ ፎቅ

ጆሴፍ ቲቶ መንገድ

ስልክ ቁጥር 0115500569

ፋክስ ቁጥር 0115158030

አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ

5. ተጫራቾች ለአገልግሎቱ የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 ( ብር መቶ ሺ) በሲፒ ኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (ጋራንቲ) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

6. የጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው፡፡

7. የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ የመቆያ ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ 90 ቀናት ነው፡፡

***ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡***

ስኳር ኮርፖሬሽን



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 22 ቀን 2012

Deadline: June 16, 2020


© walia tender

Report Page