car cater arba minch hosp2

car cater arba minch hosp2

ADMIN 3 SELAMAWIT

የጨረታ ማስታወቂያ

የደ/ብ/ብ/ሕ/መንግስት በጋሞ ዞን አርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡

ያረጁ መኪናዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ እና
አስተኝቶ ለሚያክማቸው ሕሙማን የበሰለ ምግብ ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች በየዘርፋቸው ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ሆነው ዓመታዊ የሥራ ግብር የከፈሉበትን በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትንና መረጃ ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የጨረታው ማስከበሪያ (Bid) Bond) ከሚያቀርበው ዋጋ 2% በባንክ ወይም በተረጋገጠ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
የጨረታው ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ በመደበኛ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 ለምግብ አቅራቢዎች እና 300.00 ብር መኪና መግዛት የሚፈልጉ ከሆስፒታላችን ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብና በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡

የጨረታው ዶክመንት በሰም ታሽጎ ኤንቨሎፕ አድራሻ በመጻፍ ሕጋዊ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመደበኛ የሥራ ቀናት በ 15 ኛው ቀን በ 4 ፡ 00 ሰዓት በሆስፒታላችን ግ/ፋ/ን/አስተዳደር ክፍል ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላል፡፡
ለምግብ አቅራቢዎች ተጫራቾች ለሥራው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በግላቸው በግዥም ሆነ በኪራይ ማቅረብ የሚችል መሆን አለባቸው።

ያረጁ መኪናዎችን ለመግዛት የሚፈልጉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ በመደበኛ የሥራ ቀናት በአካል ቀርበው መመልከት ይችላሉ፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ በ 8 ፡ 00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡

ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ፡በስልክ ቁጥር፡- 0468811692/0916467406 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

በደ/ ብ/ ብ/ ሕ/ ክ/ መን/ በጋሞ ዞን የአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 26 ቀን 2012

Deadline: June 17, 2020


© walia tender

Report Page