bui ABWC1

bui ABWC1

Walia Tender

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 66/2012

የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለሚገነባው ለዋናው ቢሮ ግንባታ አገልግሎት የሚውል አርምስትሮንግ አቅርቦትና ገጠማ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል"ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ አማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቀበሌ ኮብል እክሲዮን ማህበር ፊት ለፊት ቢሮ ቁጥር 11 የማይመለስ ብር 200, 00 / ሁለት መቶ ብር / በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ። የጨረታው ዉድድር በሎት/በምድብ/ ደምር ዋጋ የሚታይ ሲሆን በእንድ ሎት/ምድብ ለተጠየቁ እቃዎች ለሁሉም ዋጋ (ሙሉ ለሙሉ) ዋጋ መሞላት እንዳለበት እናሳስባለን፡፡ ነገር ግን ለድርጅቱ የተሻለ ጥቅም ያስገኛል ተብሎ ከታመነበት በድርጅቱ መመሪያ ገፅ 10 ኣንቀፅ 14.2.1 ተራ ቁጥር 4 መሰረት ውድድሩን በነጠላ ዋጋ በማወዳደር ዝቅተኛ የሆነውን በመምረጥ ግዥ ሊፈጽም ይችላል።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) ከቀኑ 8 ፡00 ሠዓት ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። 15 ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8 ፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖር ባቸዋል።
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከቀኑ 8 ፡30 ሠዓት በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 18 ይከፈታል።በሚቀርበው የጨረታ ሰነድ መሟላት ያለበት፡
3.1 በዘርፉ የንግድ ስራ ፈቃድና ለዘመኑ ስለመታደሱ ማረጋገጫ፣
3.2. ማንኛውም የወቅቱን የመንግስት ግብር ለመክፈሉ ወይም ሌሎች ግዴታዎችን ስለመወጣት ማረጋገጫ፣
3.3 የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣
3.4 የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በ ባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፣ ነገር ግን የሚያስይዘው ማስከበሪያ ከብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) መብለጥ የለበትም።
3.5 ድርጅቱ ከአሸናፊው ድርጅት ንብረቱን ከመረከቡ በፊት ናሙና አስቀርቦ የዕቃዎችን ትክክለኛነት የጥራት ቴስትበማሰራት እና በድርጅቱ አማካሪዎች በማረጋገጥ ትክከለኛነቱን ሲያሟላ ብቻ ይረከባል። ከህጋዊ ተቋማት ለሚደረግ የጥራት ማረጋገጫ ክፍያ በሻጭ ይሸፈናል።
3.6 በጨረታው ቅር የተሰኘ ተጫራች የጨረታ ውጤቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ብቻ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል።
4. በጨረታ ውድድሩ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት እቃዎችን በራሱ ወጪ ፕሮጀክቶቹ በሚገኙበት ከተማ /በሎቱ በተጠቀሰው ማስረከቢያ ቦታ ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ኣጓጉዞ ገጥሞ ያስረከባል።

5.የጨረታ አሸናፊው ለኣሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋቫትን ጨምሮ 10% የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና /የውል ማስከበሪያ/ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያስይዛል።

6. የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ45 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል።

7. የጨረታ ተወዳዳሪዎች በሌሎች ተወዳዳሪዎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችሉም።

8. በጨረታ ሠነዱ በእያንዳንዱ ገጽ እና ፖስታው ላይ የድርጅቱ ፊርማና ማህተም ሊኖር ይገባል።

9. ድርጅቱ የጨረታ አሸናፊ ከሆነው አቅራቢ የጨረታውን ይዘት ሳይቀይር ከገዛው ዕቃ መጠን ላይ በየሎቱ ጠቅላላ እቃ አይነትና መጠን ለዥ ጠቃሚ ነው ብሎ ከታመነ ውል ሲይዝ 50% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።ከውለታ በኋላ 50% ሊጨምር ይችላል።

10. ከጨረታ ሳጥን መዝጊያ ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም።

11. አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ውለታ ወስዶ ናሙና ለአማካሪ በማቅረብ ሲፀድቅለት ብቻ ኣቅርቦ ይገጥማል

12.ውድድሩ ስሎት ድምር ኣሸናፊ የሚል ቢሆንም ገዥ ድርጅቱን የሚጠቅም ሆኖ ከተገኘ በነጠላ ዋጋ በማወዳደር አሸናፊ ሊመርጥ ይችላል።

13 ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡ ለማንኛውም

ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 058-218-0711/ ፋክስ 058218-05-38/058-32-4001 /0913-10-96-11/09-12-78-30-66


የአማራ የህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 28 ቀን 2012

Deadline: June 19, 2020


© walia tender

Report Page