bu sl fr usd የሞጣ ከተማ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት
Walia Tenderግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሞጣ ከተማ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በ2013 በጀት አመት እቅድ መሰረት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግዥዎች ማለትም፡-
ሎት 1/ምድብ/ አንድ የውሃ ቧንቧ መገጣጠሚያዎችን ለመግዛት
ሎት 2/ምድብ/ ሁለት ኤሌክትሮኒክስ እና ቋሚ እቃዎችን ለመግዛት
ሎት 3/ምድብ/ ሶስት ደግሞ ባለ 6 እና ባለ 12 ሜትር ኮንቴነሮትን ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ የምዝገባ፣ የንግድ ፈቃድ እና ቲን ማቅረብ የሚችል እና የዘመኑን ግብር የከፈለበትና ማስረጃ ማቅረብ መሆን አለበት፡፡
- ተወዳዳሪው በተራ ቁጥር አንድ የተዘረሩትን ማስረጃዎች ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ ሲፒኦ ብሎ በመለየት በፖስታ በማሸግ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር እቃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ፎረም ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 በመክፈል መ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ/ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ቢሮ ቁጥር 03 በማምጣት ማስገባት ይችላል፡፡ ነገር ግን ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለበት ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ከ5 ቀናት በኋላ ከመ/ቤቱ ጋር ውል በመያዝ የአሸነፋቸውን እቃዎች ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን በ16ኛው ቀን 3፡00 ታሽጐ በእለቱ ከጠዋቱ በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስራ ሂደቱ ስልክ ቁጥር 0586611971 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሞጣ ከተማ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት ጽ/ቤት
__________________
Posted:በኩር መስከረም 18፣ 2013
Deadline:በ16ኛው ቀን 3፡00
__________________
© walia tender