bid extension1

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ ማሻሻያ
የጨረታ ቁጥር፡- ብግጨ/ ጤጥሚ/ ሆቴል/ አአ/13-2012
የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ከተማ ለሚያዘጋጃቸው ስልጠናዎችና ወርክሾፖች ለአንድ ዓመት ፀንቶ በሚቆይ ዋጋ የመሰብሰቢያ አዳራሽና የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም አዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የኮከብ ደረጃ ያላቸውን ሆቴሎች በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ከሚወዳደሩ ሆቴሎች ውስጥ ከዚህ ቀጥሎ በሰንጠረዥ እንደተመለከተው አሸናፊ ሆኖ ከሚመረጥ አንድ ሆቴል ጋር ለአንድ ዓመት ፀንቶ በሚቆይ ዋጋ የማዕቀፍ ስምምነት መፈራረም ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ከአሁን በፊት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ መጋቢት 21 እና 22 የወጣ ቢሆንም አሁን በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በመኖሩ በቂ ተሳታፊ እንዲኖር በማሰብ ጨረታውን ማራዘም አስፈልጓል፡፡

በዚህ ጨረታ ላይ የሚሳተፉ ኮከብ ሦስት ሆቴሎች ሲሆኑ ዝርዝር መመዘኛዎቹ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ መጋቢት 21 እና 22 የወጣውን መመልከት የምትችሉ መሆኑ እንገልፃለን፡፡
አድራሻ፡- ሠንጋ ተራ ጐማ ቁጠባ ፊት ለፊት
የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዋና መ/ ቤት
አዲስ አበባ
Posted: ሪፖርተር ሚያዝያ 18፥2012
Deadline: May 13, 2020
© walia tender®