bank haraj 11
አርጂ ገበያ (ጨረታ ማስታወቂያዎች)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ አማ ለሰጠዉ ብድር በዋስትና የያዘዉን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/1990 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡በዚሁ መሰረት ማንኛዉም ተጫራች ሐራጁ በሚካሄድበት ቀን ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት በጨረታዉ ተወዳድሮ ንብረቱን እንዲገዛ ተጋብዟል።



ተጫራቾች የጨረታዉን መነሻ ዋጋ 25% በባንኩ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ(cpo) አሰርቶ በጨረታዉ ቀን ይዞ በመቅረብ ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ መመዝገብ ይችላሉ።
- ጨረታዉ በማስታወቂያዉ ላይ በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ፣ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ፣ ታዛቢዎች በተገኙበት፣የመያዣ ንብረቱ በሚገኝበት የሚካሄድ ይሆናል።
- የጨረታዉ አሸናፊ ያሸነፈበትን ዋጋ ጨረታዉ ከተከናወነበት ማግስት ጀምሮ በሚቆጠር 15 ቀን ዉስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል:: በእነዚህ ቀናት ዉስጥ ካልከፈለ ግን ለጨረታ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታዉ ተሰርዞ ለሐራጅ የሚቀርብ ይሆናል።በጨረታዉ ተሳትፈዉ ላላሽነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ ወዲያኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- ኃ/የተ/የግል ማህበርን ወይም አክሲዮን ማህበርን ወክሎ መጫረት የሚፈልግ ሥራ አስኪያጅ ወይም ም/ሥራ አስኪያጅ የድርጅት የመመስረቻ ጽሑፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ይዞ መቅረብ ያለበት ሲሆን የሥራ አስኪያጅ ወይም የምሥራ አስኪያጅ ለዉጥ ተደርጎ ከሆነ ይህንኑ የሚገልጽ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የቃለ ጉባኤ ከመመስረቻ ጽሑፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ጋር ይዞ መቅረብ አለበት።
- የጨረታዉ አሸናፊ ለመንግስት የሚከፈለዉን አስፈላጊ ግብር እና ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም የሊዝ ክፍያ ይከፍላል።
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረበዉ ንብረት ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ ከጨረታዉ ቀን በፊት ባሉ የስራ ቀናት እና ሰዓት በባንኩ ጎንደር ቅርንጫፎች በመቅረብ በሚያዘጋጀዉ ፕሮግራም መሰረት ንብረቱ ያለበትን ሁኔታ መመልከት ይችላሉ።
ለተጨማሪ መረጃ አዲስ እንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ሕግ አገልግሎት በስልክ ቁጥር 0115571934፣ ጎንደር ቅርንጫፍ 0581115503/0237 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ አማ.
Posted date:ሪፖርተር መጋቢት 13፥2012
Dead line:April 22,2020(ሚያዝያ 14)