Yenetube

Yenetube


ግብጽ እና ኢትዮጲያ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የጀመሩት ድርድር ካልተሳካ ወታደራዊ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ የግብጽ መገናኛ ብዙሃን ግፊት ማድረጋቸወን ቀጥለዋል።

አምስት ቢሊየን ዶላር እንደሚፈጅ በተነገረለት እና ሰባ በመቶም ግንባታው በተጠናቀቀው ግድብ ዙሪያ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የተደረገው ውይይት ያለስኬት ተጠናቋል፡፡ ግንባታው ሲጠናቀቅ ለአንድ መቶ ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን የሚያስፈልገውን የኤሌክትሪክ ሃይል ፍላጎት እንደሚያሟላ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

ከኢትዮጲያ ተቃራራቢ የሕዝብ ብዛት ያላት ግብፅ የግድቡን የውሃ ማጠራቀሚ የመሙላት ሂደት የግብጽን የውሃ ድርሻ ይቀንሰዋል የሚል ስጋት አላት፡፡

የእስራኤሉ ዘ ታየምስ ኦፍ አስራኤል የተሰኘው የህትመትና የድረገጽ ሚዲያ ሰፋ አደርጎ ባወጣው ሀተታ ለመንግስት ቅርበት እንዳለው የሚነገርላቸው የግብጽ መገናኛ ብዙሃን ግድቡ ለግብጽ ብሔራዊ ደህንነት ስጋት ስለሆነ መንግስት ወታደራዊ እርምጃ ሊወስድ ይገባል በማለት ግፊት እያደረጉ ይገኛል፡፡

የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ ኤል ሲሲ ባለፈው ወር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባደረጉት ንግግር ኢትዩጵያ ግድቡን ያለስምምነት እንድትሞላ ፈጽሙ አንፈቅድም” ማለታቸው ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያን የመልማት መብት አምነን የምንቀበል ቢሆንም የአባይ ወንዝ ውሃ ለግብፅ የህልውና ጥያቄ ነውም ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በተመሳሳይ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር “የአባይ ወንዝ አጠቃቀም መወሰን ያለበት በዓለም አቀፍ ሕግ እና የተፈጥሮ ሀብቶችን በፍትሃዊ መንገድ በመጠቀም መርህ ነው” ብለዋል ፡፡

ግብፅ የዓባይ ወንዝ ከፍ ያለውን ድርሻ እየተጠቀመች ነው በሚል የላይኛው ተፋሰስ ሃገራት ኢትዮጲያ እና ሱዳን ለዓመታት ሲያቀርቡ የነበረውን ቅሬታ የምትሞግተው በብሪታኒያ የቅኝ ግዛት ዘመን የተፈጸሙ ስምምነቶችን በማጣቀስ ነበር ፡፡

በዚህ ወር መጀመሪያ ያለስኬት የተጠናቀቀው ውይይት እ.ኤ.አ. ከ 2014 በኋላ ለሶስተኛ ጊዜ የተከናወነ ነበር ፡፡

አንድ የግብጽ ባለስልጣን ከአሶሺየትድ ፕሬስ ጋር ባደረጉት ቆይታ “ጊዜያችንን ትርጎም በሌላቸው ውይይቶች አናጠፋም ፡፡ ሁሉም አማራጮች ጠረጴዛው ላይ አሉ፡፡

ምርጫችን ግን ድርድር እና ፖለቲካዊ መፍትሄ ነው” ማለታቸውም ተነግሯል ፡፡

ግብፅ በዓለም አቀፍ አሸማጋዮች ከተሻለ ስምምነት እደርሳለሁ በሚል ጉዳዩን ወደ አሜሪካ ሩሲያ ፣ ቻይና እና አውሮፓ ህብረት ወስዳዋዋለች፡፡

ዋይት ሀውስ “አንዳቸው የሌላውን የናይል የውሃ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት መብት በማክበር ከዘላቂ ስምምነት ለመድረስ የሚያደርጉትን ውይይት እንደሚደግፍ” በዚህ ወር መጀመሪያ አስታወቁል፡፡

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን መሃመድ ኢል ሞላ ኢትዮጵያውያን ዓለም አቀፍ ሽምግልናን ካልተቀበሉ ጉዳዩን ለተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት እንደሚወስዱ ተናግረዋል ፡፡

በብራስልስ መሰረቱን ያደረገ አንድ የዓለም አቀፍ ቀውስ ላይ አሰላሳይ ቡድን ፣ “የሁለቱ አካላት የመዳረሻ ወንዝ አስተዳደር ላይ ካልተስማሙ ለወደፊቱ ግጭት የመጋለጥ እድላቸው ሰፊና ከባድ ሊሆን ይችላል” ሲል በዚህ ዓመት መጀመሪያ ቀደም ብሎ አስጠንቅቆ ነበር፡፡

ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በግብፅ ተቃዋሚ መንግስት ሚዲያዎች እና አንዳንድ ተንታኞች መንግስት በጉዳዩ ላይ በኃይል እንዲቀሳቀስ ጥሪ አቅርበዋል፡፡


ለዕለታዊ ጋዜጣ ኤል-ሾሮክ ታዋቂው አምድ አዘጋጅ የሆኑት አብደላ ኤል-ሴናው እንደተናገሩት ብቸኛው አማራጭ አለመግባባቱን ዓለም አቀፍነት በማረጋገጥ ወይም ወታደራዊ እርምጃ በመውሰድ ላይ ነው ብለዋል ፡፡

በእሁዱ እትም ላይ “ግብፅ አነስተኛ ግዛት አይደለችም” ሲል ጽፏል ፡፡ ሁሉም ዲፕሎማሲያዊ እና ህጋዊ አማራጮች ከከሸፉ ወታደራዊ ጣልቃገብነት አስገዳጅ ሊሆን ይችላል ሲልም አስፍሯል ፡፡

የአል-ማሳሪ አል-ዮየም ጋዜጣ የቀድሞው አምደኛ አንዋር ኤል ሃውሪር ግብፅ በሲና ባሕረ ገብ መሬት ድንገተኛ ጥቃት ከፈፀመችበት የ 1973 ዮም ኪፑር ጦርነት ጋር በማነፃፀር ፡፡

በፌስቡክ ገጹ ላይ “ሲናን ለመልቀቅ ከታገልን ውሃውን ነፃ ለማውጣት መዋጋት ምክንያታዊ ነው” ሲል ጽፏል ፡፡ በሁለቱ ጉዳዮች ላይ “አደጋው ተመሳሳይ ነው ፡፡ የመጨረሻው ምላሽ ደግሞ ጦርነት ነው ይላል፡፡

ግብጽ በኢትዮጵያ ህዳሴ ግድቡ ዙሪያ መውሰድ ስላለባት እርምጃ ለማማከር የተቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ ዛሬ የመጀመሪያውን ስብሰባ እንደሚያደረግ ይጠበቃል።

ፕሬዘዳነት አልሲሲ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ መውሰድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች የሚያማክረው ቡደን ባሳለፍነው እሁድ አመሻሽ የመጀመሪያውን ስብሰባ ማድረጉ ይታወሳል።

ይህ ቡድን የግብጽን ታሪካዊ የውሃ ድርሻ ይጋፋል በሚል ከአንድ ሳምንት በፊት ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጣ ብሄራዊ አማካሪ ምክር ቤት ነው።

የዚህ ቡድን ዋና አላማ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብ የግብጽን ታሪካዊ የውሃ ድርሻ የሚጎዳ በመሆኑ ፕሬዘዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ የግብጽን ጥቅም ለማስበር መውሰድ ስለሚኖርባቸው እርምጃዎች ማማከር መሆኑ ተገልጿል።

ነገ በሩሲያዋ ሶቺ ከተማ ለሚካሄደው የአፍሪካ ሩሲያ ጉባኤ ላይ ለመታደም ወደ ስፍራው ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከግብጹ ፕሬዘዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ጋር ከጉባኤው ጎን ለጎን በህዳሴው ግድብ ቀጣይ ድርድር ዙሪያ እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

Via:- EthioFM

@Yenetube @Fikerassefa

Report Page