Yenetube

Yenetube


የቅጥር ማስታወቂያ

______________

ባህር ዳር ታህሳስ 18/2012 ዓ.ም የአመራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በመደበኛ ፖሊስነት እና የአድማ መከላከል ፖሊስ ተቀጥሮ ለማገልገል ፍቃደኛ የሆኑ ወጣቶችን በትምህርትና ስልጠና መመልመያ መስፈርቱ መሰረት በመመልመል ቀጥሮ በማሰልጠን ወደ ስራ ማሰማራት ይፈልጋል፡፡

-

ተመልማዮቹ ምልመላው ተጠናቆ ወደ አማራ ፖሊስ ኮሌጅ (ደ/ማርቆስ) ገብተው ሥልጠና ከመጀመራቸው በፊት የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 216/2006 እና ይህን ለማስፈፀም በሥራ ላይ ባሉ ደንብና ልዩ ልዩ መመሪያወች መሠረት የ7 ዓመት የሥራ ውል ግዴታ በመግባት በፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋሙ አማካይነት የሚሰጣቸውን ሥልጠና መከታተል አና በሚገባ ማጠናቀቅ የሚጠበቅባቸው ሲሆን በሥልጠና ቆይታ ጊዜያቶችም የምግብ፣ የመኝታ፣ የሕክምና እና ለሥልጠናው የሚያስፈልጉ የአልባሳት፣ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችና የኪስ ገንዘብ ይሰጣል።

-

ሥልጠናው ሲጠናቀቅም እያንዳንዱ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ በየወሩ 1975 /አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ አምስት ብር / ወርሃዊ ቀለብ 850.00 / ስምንት መቶ ሃምሳ ብር / በድምሩ 2825 ብር ሲሆን ልዩ ልዩ የስራ አልባሳት በተቋሙ እና የሕክምና አገልግሎትን ደግሞ በፖሊስ ክሊኒኮችና በፖሊስ ሆስፒታል በነፃ ያገኛሉ።

-

ተመርቀው ፖሊሳዊ የሙያ አገልግሎት በሚያበረክቱባቸው ጊዜያትም በተቋሙ ውስጥ በአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ፣ ደንብ እና የሥልጠና መመሪያዎች መሠረት በሚወጡ መመዘኛዎች አማካይነት በልዩ ልዩ የትምህርትና ሥልጠና ፕሮግራሞች እራሳቸውን ለተወዳዳሪነት በማዘጋጀት እየቀረቡ ተጠቃሚ የመሆን ሠፊ ዕድል የሚጠብቃቸው መሆኑን የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን በደስታ ይገለፃል።

-

የመመልመያ መስፈርቶች

-

1. ዜግነት ኢትዮጵያ የሆነ/የሆነች፣

2. ለህገ-መንግስቱ ታማኝና ተገዢ የሆነ/የሆነች፣

3. ከማንኛውም ደባል ሱስ ነፃ የሆነ/ች፣

4. ፖሊስ ሆኖ ለመስራት ፍላጎት ያለው/ያላት/ እና ለመሰልጠን ፈቃደኛ የሆነ/ች፣

5. በመልካም ስነ-ምግባሩ/ሯ የተመሰከረለት/ላት፣

6. በማንኛውም ወንጀል ተከሶ ያልተቀጣ/ች፣

7. የትምህርት ደረጃው 10ኛ/12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ች፣

8. ዕድሜ ከ18 አመት ያላነሰ/ች/ ከ25 አመት ያልበለጠ /ች፣

9. ኮሌጁ በስልጠና ወቅት የሚያቀርበውን ምግብ ለመመገብ ፈቃደኛ የሆነ/ች፣

10. የተሟላ ቁመናና ጤና ያለው/ላት መሆኑ በህክምና ማስረጃ የተረጋገጠ፣

11. ቁመት ለወንድ 1.65 ሳ.ሜ ሴት 1.55 ሳ.ሜትርና በላይ የሆነ/ች፣

12. ክብደት ወንድ ከ50.ኪ.ግራም ያላነሰ ከ70.ኪ.ግራም ያልበለጠ ሴት ከ45 ኪ.ግራም ያላነሰች ከ65 ኪ.ግራም ያልበለጠች፣

13. ሴት ተመልማዮች ከእርግዝና ነፃ ማረጋገጫ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በኮሌጁ ህክምና በድጋሜ የሚረጋገጥ ይሆናል፣

14. በክልሉ ውስጥ በየትኛውም ዞን፣ ወረዳ፣ ቀበሌ/ቦታ ተመድቦ ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ/ች፣

15. በክልሉን የስራ ቋንቋ መፃፍና መናገር የሚችል/የምትችል፣

16. ከስልጠና በኃላ 7 አመት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ/ች፣

17. የምዝገባ ቦታ በሁሉም የክልሉ ወረዳዎች ይከናወናል

18. የምዝገባ ጊዜ ከታህሳስ 19/2012 እስከ ጥር 05/2012 ዓ.ም ይሆናል፡፡

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን

ባህር ዳር

Report Page