YYenetube

YYenetube


የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ ስብሰባ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ ስብሰባ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

ለሁለት ቀናት በባሕር ዳር ከተማ ሲካሄድ የቆየው የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ መክሯል፡፡

የመማክርት ጉባኤው በዋናነት የአማራ ሕዝብ በሚያነሳቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ በስፋት ሲመክር ቆይቷል፡፡

ዛሬ ጉባኤው ሲጠናቀቅም ባለዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

በዚህ የአቋም መግለጫ ከተካተቱ ሀሳቦች መካከልም ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ያሳተፈ፣ የፌዴራሊዝም ሥርዓትን የሚያጠናክር ሕገ መንግሥታዊ ማሻሻያ እንዲደረግ የሚጠይቀው ይገኝበታል።

የሕዝቦችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ፣ ሁሉም ቋንቋዎችና ባሕሎች እንዲበለፅጉ በሚያግዝ መልኩም ማሻሻያው እንዲከናወንም ነው የመማክርት ጉባኤው የጠየቀው፡፡

ዲሞክራሲ፣ ፍትህ እኩልነትና ነፃነት እንዲሁም ብልፅግና የሰፈነባት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግም ከሌሎች ወንድምና እህት ኢትዮጵያውያን ጋር ይበልጥ ተባብሮ ለመስራት መወሰኑንም በመግለጫው አንስቷል፡፡

የህዝቡ ፈታኝ ችግር የሆኑትን የስራ አጥነትና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስም የክልሉንና የመላ ኢትዮጳያን እምቅ አቅምና ክህሎት በመጠቀም ይሰራል ነው ያለው፡፡

ከዚህ አስቀድሞ በሁለቱ ቀናት ለውይይት የቀረቡ አራት ጥናታዊ ጽሑፎችን መነሻ በማድረግም ከተሳታፊዎች በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በቀጣይም ከህበረተሰቡ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት ይቻል ዘንድ በየደረጃው ውይይት ይደረጋል ተብሏል፡፡

በውይይቱ 1 ሺህ 800 ምሁራንና ከ700 በላይ ተጋባዥ እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Via:- Walta

@YeneTube @Fikerassefa

Report Page