What are Polyphenols?
Crohn's & Colitis Ethiopia
የpolyphenols የጤና በረከቶች
polyphenols በተለያዩ ምግቦች ውስጥ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያላቸው ንጥረ ነገሮች ናቸው፡፡ ከነዚህ ጠቀሜታዎች ውስጥ፡-
ü የሰውነትን ክብደት ማስተካከል፤ በሰውነታችን ውስጥ ያሉ የስብ ክምችቶች ወደ ገንቢ ንጥረ ነገሮች እንዲቀየሩ በገንቢ አፍራሽ ቅንባሮ ሂደት( metabolism) ውስጥ ማለፍ አለባቸው፡፡ polyphenols ይህንን ሂደት በማፋጠንና በሰውነታችን ውስጥ ያለን የስብ መጠን በመቀነስ የሰውነታችንን የክብደት መጠን እንድንቆጣጠረው ይረዱናል፡፡
ü ሰውነታችን በደማችን ውስጥ ያለውን የግሉኮስ መጠን ከጣፊያችን በሚለቀቅ ኢንሱሊን በተባለ ንጥረ ነገር ይቆጣጠራል፡፡ polyphenols ደግሞ በሰውነታችን ውስጥ ያለውን ግሉኮስ ( ስኳር ) የመፈጨትና ለሰውነት ጥቅም የማዋል ሂደት በማስተካከልና በመቆጣጠር ጤነኛና የተስተካከለ የኢንሱሊን ስርዓት በሰውነታችን ውስጥ እንዲኖረን ይረዱናል፡፡ ይህ ደግሞ ሰውነታችን አስፈላጊውን የሃይል መጠን እንዲያገኝ ይረዳዋል፡፡ ለዚህም ነው የpolyphenols የምግብ ምንጮችን የሚመገቡ ሰዎችና በየእለቱ የሰውነት እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሰዎች ምንም እንኳ በከባድ የሰውነት ጉልበትን የሚፈትኑ ውሎዎች ውስጥ ቢያልፉም ጉልበታቸው እንዳለ የሚቆየውና የማይዳከሙት፡፡
ü polyphenols የሰውነት መቆጣትንና ቁስለትን ይቀንሳሉ፡፡ የpolyphenols የምግብ ምንጮችን አዘውትረው በሚመገቡ ሰዎች ላይ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በሰውነታቸው ውስጥ የሰውነት መቆጣትን የሚያስከትሉ ነገሮች መጠን ቀንሶ ታይቷል፤ ከዚያም በተጨማሪ በሰውነታቸው ውስጥ ያለው የኮሌስትሮል መጠንም አነስተኛ ነው፡፡
ü ላለፉት 20 አመታት የተደረጉ ጥናቶች ፤እነዚህ ውህዶች እንደ የልብ ህመም፣ የአጥንት መሳሳት ና ካንሰር ያሉ ስር የሰደዱ ህመሞችን ለመከላከል ትልቅ አስተዋፆ እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡
ü የእነዚህ የpolyphenols ከላይ የተጠቀሱት አይነት የጤና በረከቶች ውጤታማነት የሚወሰነው በምንመገበው ምግብ ውስጥ ያለው የ polyphenols መጠንና የሰውነታችን እነዚህን ንጥረ ነገሮችን የመምጠጥና የማጠራቀም አቅም ላይ ነው፡፡ ስለዚህም እነዚህ ንጥረ ነገሮች ወደ ሰውነት የሚመጠጡበት መጠን ከሰው ሰው ስለሚለያይ ለሁሉም ሰው የሚስማማና በቀን ውስጥ ይህን ያህል የ polyphenols መጠን ያላቸው ምግቦችን መመገብ አለብን የሚባል የተመደበ ልኬት የለም፡፡
በ polyphenols የበለፀጉ ምግቦች
polyphenolsን ከተለያዩ ከእፅዋት ከሚገኙ ምግቦች ውስጥ እናገኛቸዋለን፡፡ ከእነዚህም መካከል
v አትክልቶች ፡- የ polyphenol መጠናቸው ከፍተኛ ነው፤ ከእነዚህም መካከል አበባ ጎመን፣ ካሮት፣ ቆስጣ፣ሽንኩርት፣ነጭ ሽንኩርትና ቀይ ሰላጣ ይገኙበታል፡፡
v ፍራፍሬዎች ፡- በpolyphenols ከበለፀጉ ፍራፍሬዎች መካከል እንጆሪ( ቀይ፣ሰማያዊ፣ጥቁር) ፣ወይን፣ሎሚ፣ብርቱካን፣አፕል፣ኮክና የወይራ ፍሬ ይጠቀሳሉ፡፡
v ጥራጥሬዎች፡- የpolyphenol መጠናቸው ከፍተኛ ከሆነ ጥራጥሬዎች መካከል አጃ ና ስንዴ ይጠቀሳሉ፡፡
v የቅባት እህሎች፡- ለውዝ ናተልባ በ polyphenol ከበለፀጉ የቅባት እህሎች ውስጥ ይጠቀሳሉ፡፡
v ሌሎች አዝርዕት፡- ቦሎቄ፣ ባቄላ( ጥቁር፣ ነጭ) እና አኩሪ አተርም የ polyphenols መጠናቸው ከፍተኛ ነው፡፡
v ቅመማ ቅመሞች ፡- እርድ፣ቀረፋ፣ከሙን፣ቅርንፉድ፣ጅንጅብል፣የሾርባ ቅጠል፣የመጥበሻ ቅጠል፣ጦስኝ፣ ሰሊጥ፣በሶቢላ፣በርበሬና ኮሰረት የ polyphenols መጠናቸው ከፍተኛ ከሆኑ ቅመማ ቅመሞች ውስጥ ይጠቀሳሉ፡፡
v ሌሎች ፡- ከላይ ከተጠቀሱት ውጪ ያሉ በ polyphenols ከበለፀጉ ምግቦችና መጠጦች ውስጥ፤ አረንጓዴ ሻይ፣ ቀይ ወይን፣ጥቁር ቸኮሌት ና ቡና ይጠቀሳሉ፡፡
በሚቀጥለው ሳምንት በሻይና በpolyphenols ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያን ይዘን እንቀርባለን፡፡ ይከታተሉን!
07/05/2022
Crohn's & Colitis Ethiopia
References:
- Pérez-Jiménez, J., Neveu, V., Vos, F. et al. Identification of the 100 richest dietary sources of polyphenols: an application of the Phenol-Explorer database. Eur J Clin Nutr 64, S112–S120 (2010). https://doi.org/10.1038/ejcn.2010.221
- Cory H, Passarelli S, Szeto J, Tamez M and Mattei J (2018) The Role of Polyphenols in Human Health and Food Systems: A Mini-Review. Front. Nutr. 5:87. https://doi: 10.3389/fnut.2018.00087