Walua tender 8

Walua tender 8


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡- አአትማኤ/ ብግጨ/ ግዳ/ ስራ/026/2012

የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ በ2012 የበጀት ዓመት ለኤጀንሲው አገልግሎት የሚውሉ አምስት (5) ሚኒባሶች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም :- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ፤

የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 300.00 ( ሶስት መቶ ብር ) የማይመለስ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣ ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ዘወትር በስራ ሰዓት ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡30 ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 10፡00 ከኤጀንሲው ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10-02 መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለሚያቀርቡት ዕቃ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣
ተጫራቾች በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፣
ተጫራቶች ለጨረታው ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ( ሲፒኦ) ተመላሽ የሚሆን 100,000.00 ( መቶ ሺህ) ብር ማስያዝ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ጨረታ በመለየትና በፖስታው ላይ በመግለጽ አስፈላጊዎቹን መረጃዎች ሁሉ በማካተትና በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 100 ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ እስከ ሚያዝያ 28/2012 ዓ . ም ከቀኑ 8 ፡ 00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፣
የጨረታው አሸናፊ ሆነው የተመረጡት ድርጅቶች የጨረታው ውጤት በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በአስር የሥራ ቀናት ውስጥ ኤጀንሲው ግዥ ዳይሬክቶሬት ዋና ክፍል በመቅረብ ያሸነፈበትን ዋጋ 30% የመልካም ሥራ አፈፃፀም በማስያዝ ውል መፈረም አለባቸው፣
የጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች በፈረሙት ውል መሠረት በራሳቸው ትራንስፖርት አሸናፊ የሆኑባቸውን አገልግሎቶች ኤጀንሲው ፕሮጀክት ቦታ ድረስ ማቅረብ አለባቸው፣
ጨረታውን አሸናፊ ላልሆኑ ድርጅቶች በጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ የአሸናፊነት ደብዳቤ ከተሰጠው በኋላ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል፣
ጨረታው ሚያዝያ 28/2012 ዓ . ም በ 8 ፡ 00 ሰዓት ይዘጋል፣
ጨረታው ሚያዝያ 28/2012 ዓ . ም ከቀኑ በ 8 ፡ 30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም ፡፡
ኤጀንሲው ጨረታውን በተመለከተ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- ሃያ ሁለት መክሊት ህንፃ 10 ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10-01

ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥሮች፡- 0116-672342 ማነጋገር ይችላሉ።

የ አዲስ አበባ ከተማ መንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ


Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 17፥2012

Deadline: May 6, 2020


back


Report Page