Walua tender 13

Walua tender 13


በድጋሚ የወጣ የማባዣ ቀለም ግዥ

ጨረታ ማስታወቂያ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2012 በጀት ዓመት ለዩኒቨርሲቲው አገልግሎት የሚውሉ የማባዣ ቀለም በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ አውጥተው ከተሰማሩ ህጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

ዘርፉ የወጣና ለዘመኑ የታደሠ የንግድ ሥራ ፈቃድ ኮፒ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ኮፒ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ኮፒ፤ በእቅራቢነት በኤጀንሲው ድረ-ገጽ የተመዘገቡ፤ በማንኛውም የመንግስት ግዥ ጨረታ እንዲሳተፉ በሃገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የተሰጠ የድጋፍ ደብዳቤ ኮፒ፤ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የገቡበት ቅጽ ሞልተው ፈርመው እና በድርጅታቸው ማህተም አረጋግጠው ዋናውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ብር 80,000.00 / ሰማንያ ሺ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይ ም ከታወቀ ባንክ ስሚሰጥ ሲፒኦ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም ስሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስም አሰርተው ማቅረብ አለባቸው:: በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ከ88 ቀን በታች መሆን የለበትም፡፡
ተጫራቾች በተራቁጥር 1 እና 2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ እንዲሁም የዋጋመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ተለይቶ በተለያየ ፖስታ በማሸግና በማያሻማ ሁኔታ በጀርባው ላይ ፋይናንሻል ኦርጂናል እና ፋይናንሻል ኮፒ በሚል ቃል ስጽሁፍ በማመላከትና በድርጅታቸው ማህተም በማረጋገጥ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ሁሉም /ሶስቱም/ ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ ተጠቃልለው ታሽገውና በድርጅቱ ማህተም ተረጋግጠው መግባት አለባቸው።
ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፋይናንስና በጀት ዳይሬክቶሬት ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 07 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመምጣት የማ ይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመከፈል መውሰ ድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነዳቸውን ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ይህ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታውም ታዛቢዎችና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት 4 ፡01 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 4 ፡10 ሰዓት ጀምሮ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ህንፃ ላይ በሚገኘው የስልጠና ( ኤች. ዲፒ) አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም 16 ኛው ቀን የህዝብ ወይም የሃይማኖት በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ 60 ቀን ድረስ ጸንቶ መቆየት አለበት፡፡
ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታከስ እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋ ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ የታክስ ሁኔታ ያልተገለጸ ከሆነ የተሞላው ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ታክስና ወጭን አካትቶ እንደተሞላ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያያዘው ስፔስፊኬሽን በተጨማሪ ናሙና ማቅረብ አለባቸው::
ለተጨማሪ መረጃ ስል ክ ቁጥር 0582118084 ወይም 0582116092 በስራ ሰዓት በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ



Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 17፥2012

Deadline: May 10, 2020



back


Report Page