Waliabtender 23

Waliabtender 23


የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 26/2012

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ሱሉልታ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ሱሉልታ ቅርንጫፍ ዴፖ ጽ/ቤት የተለያዩ የሲቪል የግንባታ ሥራዎች ለኮንስትራክሽን ስራዎች የሚውል በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ በተዘጋጀው መደበኛ የጨረታ ሰነድ መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ደረጃ 5 እና ደረጃ 4 የሆኑ ሥራ ተቋራጮች መወዳደር ይችላሉ

ተጫራቾች የሚከተሉትን ሠነዶች ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት (VAT)፣ የግብር ከፋይነትሠርተፍኬት (TIN)፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና ስለ ግብር አከፋፈል የተሰጠ ማስረጃ
በተቁ 1 ከተጠቀሱት በተጨማሪ ተጫራቾች ደረጃቸውን የሚገልጽ - የታደሰ የምስክር ወረቀት፣ ለሥራው የሚያስፈልጉ መሣሪያዎችና ተሽከርካሪዎች ዝርዝር መግለጫ ለሥራው የሚያስፈልጉ የባለሙያዎች መግለጫና ዝርዝር እና በጨረታው ለተጠየቀው ሥራ ወይም ተመሳሳይ የሥራ ልምድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ብር 250,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች አንድ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ የመወዳደሪያ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 18/09/2012 _ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 602 ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው በዚሁ ቀን 18 /09/2012 ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4 ፡05 ሰዓት ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 602 ይከፈታል፡፡
ተጫራች የሥራውን ዓይነትና ሁኔታ በአካል በመገኘት ማየትና ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ
ተጫራች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ከድርጀቱ ግዥና ትራንስፖርት ክፍል ቢሮ ቁጥር 006 መውሰድ ይችላሉ፡፡
ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በመሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 011-551-32-88

አድራሻ፡- ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሣርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት


Posted: አዲስዘመን ሚያዝያ 16፥2012
Deadline: May 26, 2020


back

Report Page