Walia trnder bole w 9

የግልፅ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 001/2012
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን
ሎት 1. የአላቂ የፅሕፈት መሣሪያዎች፤
ሎት 2. የህትመት ውጤቶችን፤
ሎት 3. የፅዳት እቃ
ሎት 4 መድኃኒትና የሕክምና እቃ
ሎት 5. አላቂና ቋሚ የቢሮ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 100 / አንድ መቶ ብር/ በመ ክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 403 እያቀረቡ መግዛት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች በዘመኑ የተሰማሩበትን ህጋዊ የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ከጨረታው መቅረብ የሚያስችል ክሊራንስ ማቅረብ የሚያስችል።
ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

6.ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 403 በመምጣት የዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
7. ጨረታው በ10 ኛው ቀን ታሽጎ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከቀኑ 4 ፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ የሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
8. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።
9. ተጫራቶች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መሥሪያ ቤቱ ባቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ያላቀረቡባቸውን ዕቃዎች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
10.የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት እስከ መ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
11. መስሪያ ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨምር መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ጎሮ መስጊዱ ጀርባ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት፡፡
ስልክ ቁጥር 011-8-63-73 90
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 የጎሮ ጤና ጣቢያ
_______________________________
Category : Cleaning and Janitorial., Cleaning and Janitorial Equipments, Medical Equipment and Supplies, Pharmaceutical Products/Medicines, Medical/Laboratory Equipment, Office Supplies and Stationery, Office Items and Equipment, Stationery Supplies, Printing and Publishing., Printing and Publishing Service, Purchase.
Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 6 ቀን 2012
Deadline :2020-03-24[መጋቢት 15]
Back to home