Walia tender subsc aau

Walia tender subsc aau


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በ2012 በጀት ዓመት ለኮሌጁ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ

በዚሁ መሠረት ብቃት ያለውና ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው ተጫራች የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200 ( ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የምትጫረቱበትን የጨረታውን ሰነድ በመግዛት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዚህ በታች በቁጥር 8 «» በተገለፀው አድራሻ መሰረት 29 እና 25 ቀን 2012 ዓም በ8 ፡00 ሰዓት ወይም በፊት በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 001 በመቅረብ ማስገባት ይቻላል፡፡

1. ጨረታው የሚከናወነው ብቁ በሆኑ አምራቾች ወይም አቅራቢዎች ሆኖ ማንኛውም ተጫራች ፣ (ሀ) የታደሰ የንግድ ፈቃድ (ለ) የግብር ከፋይ የምስክርነት (ወረቀት (ሐ) የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት (መ) የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚፈጽሙት ግዥ ለመሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ የምስክርነት ወረቀት (ሠ) ወቅታዊ የሆነ የታክስ ከሊራንስ (ረ) ላለማጭበርበር ቃል የሚገባበት ቅጽ ፈርሞ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በCP0 ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡

3. ጨረታው የሚከናወነው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ግዥ አዋጅ በተገለፀው የብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ ሥርዓት መሠረት ይፈጸማል፡፡

4 በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሠረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በጨረታ ማስከበሪያ፣በውል ማስከበሪያ እና በቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ምትክ ተቋማቱን ካደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡

5 ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሲያቀርብ በሁለት ኤንቨሎፕ ሆኖ ዋናውና ቅጂው ላይ ስልጣን ባለው አካል መፈረምና ማህተም መደረግ አለበት

6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታው መዝጊያ ከተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ዘግይቶ ሲመጣ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

7. የጨረታው ሰነድ የሚላከው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ግዥ ክፍል ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት ይሆናል፡፡

8. የጨረታ ሠነድ በተመለከተ፡

ሀ/ ሰነዶች የሚወሰዱት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 001 ለ ጨረታው የሚከፈተው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር: 001 ይሆናል

9. ጨረታው መጋቢት 29 እና 25 ቀን 2011 ዓ. ም ከሰዓት 8 ፡00 ሰዓት ታሽጎ 8 ፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጅ ግዥ ክፍል ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡

10 መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በመሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡-0111260568 /0111542227

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስና

ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ


______________________________

Category : Cleaning and Janitorial., Cleaning and Janitorial Equipments, Electrical and Electronics, Electrical Equipment and Accessories, Electronics Equipment, Installation and Maintenance, Office Supplies and Stationery, Stationery Supplies, Plastic/ Pipes and Fittings, Pipes and Tubes, Printing and Publishing., Printing and Publishing Equipment/Appliances, Purchase., Vehicle and Spare Parts, Tyre and Battery
Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 8 ቀን 2012
Deadline :2020-04-07 [መጋቢት 29]




Back to home

Report Page