Walia tender subs haraj

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት እነ አቶ አወል ይማም እና በፍ/ባለዕዳ እነ ሙክታር አብደላ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 106638 በ19/30/2008 ና በመ/ቁ 152768 በ28/3/2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ቦሌ ክ/ከተማ ወ/4 የቤቁ 5023 የሆነ ቤት በቁጥር ቦሌ 14/30/8/14898/240/18/00 የተመዘገበ ካርታ ያለው ከማህደራቸው ውጪ ያልሆነ የይዞታው ስፋት በልኬት 140 ካሜ ወጪ ባልሆነ ካርታ ላይ 120 ካሜ ግምቱ 411,440 (አራት መቶ አስራ አንድ ሺህ አራት መቶ አርባ ሆኖ ሚያዚያ 21 ቀን 2012 በ8፡30 ሰዓት 2ኛ በኦሮሚያ ክልል ሰበታ ከተማ ቀበሌ 02 ያለቤት የሐራጅ መነሻ ዋጋ 143,997.53 (አንድ መቶ አርባ ሶስት ሺ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት ከ53/100 ) በቁጥር ሰ/1122/97 የተመዘገበ ካርታ ያለው የቦታው ስፋት 160 ካሜ መሆኑ ታውቆ ሚያዚያ 21 ቀን 2012 በ8፡30 ሰዓት የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 411,440 (አራት መቶ አስራ አንድ ሺ አራት መቶ አርባ ብር ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሚያዚያ 21 ቀን 2012 ዓ. ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቶች ምዝገባ በ8 ፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቶች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቶች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በተጨማሪ ተጫራቶች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጉድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬቱ የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የፌዴራል ፍ/ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት
_______________________________
Category : Foreclosure., House and Building Foreclosure, House and Building., House and Building Sale, Sale.
Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 10 ቀን 2012
Deadline :2020-03-29 [መጋቢት 20]
______________________
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የቤ.ቁ … የሚገኝ ኮንዶሚኒየም ቤት ስፋቱ 44-60 ካሜ ካርታ ያለው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 178,400.00 መሆኑ ታውቆ ሚያዝያ 16 ቀን 2012 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡|በኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት
Deadline: April 24, 2020 [ሚያዝያ 16]
[አዲስ] በቦሌ ክ/ከተማ ወ/07 … የሚገኝ የሠ/ቁ 3-A04… አ.አ የሆነው መኪና የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 155,000 መሆኑ ታውቆ ሚያዚያ 14 ቀን 2012 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡|የኢፌዲሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት |
Deadline: April 22, 2020 [ሚያዝያ 14]
back to foreclosure
back to home