Walia tender sub mes ed sch

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 ስር የሚገኘው የመሠረተዕድገት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2012 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ እቃዎች በግልፅ ጨረታ ቁጥር 002/2012
ሎት 1. የደንብ ልብስ
ሎት 2 የቢሮ እቃዎች
ሎት 3 ህትመቶች
ሎት 4 የፅዳት እቃዎች
ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ እና የቧንቧ እቃዎች
ሎት 6 ቤተ ሙከራ
ሎት 7 መማርያ መፅሐፍት
ሎት8 ህክምና እቃዎች
ሎት 9 የጥገና እቃዎች
በዚሁም መሰረት በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባወጣው የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል። ለዚሁም በመስኩ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውናቫትተመዝጋቢ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የተደራጁ ጥቃቅን እና አነስተኛከሆኑ ካደራጃቸው አካል ወቅታዊ የሆነ የድጋፍ ደብዳቤ በት/ቤት ስም በቅድሚያ ማጻፍ አለባቸው፡፡ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና ደብዳቤ በት/ ቤቱ ስም በትክክለኛ አድራሻ ከሚመለከታቸው አካል ማጻፍ አለበት።
ተጫራቾች የቲን መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውንጨረታ ሰነ ድ የማይመለስ ብር 150/ አንድ መቶ ሃምሳብር/ በመክፈልከት/ ቤቱ ዥ ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
ማንኛውምተጫራችበሰነዱላይናሙናእንዲቀርብባቸው ለሚጠየቁ ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለበት፡፡
ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
አሸፊናፊው እንዴታውቀ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበርያ (የጨረታ ዋስትና) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የአሸናፊነት ደብዳቤ ከተገለፀበት እስከ 7 ቀን በኋላ ቀርቦ ውል ካልፈረመ ለጨረታ ያስያዘው ገንዘብ ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረግ፡፡
ጨረታው ከመዘጋቱ ከ5 ቀን በፊት ማንኛውም ጊዜና ሰዓት ጨረታውን ያወጣው አካል የጨረታ ሰነዱን ከተጫራቾች በሙሉ በማሳወቅ ሰነዱን ማሻሻል ይችላል፡፡
ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋቫትን ጨምሮ በታሸገ እና ማህተም ባረፈበት ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ በት/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ ላይ ከወ ጣበት ቀን ጀምሮ በ11 ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት በ4 ፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ካልተገኙ የመስረያ ቤቱ የጨረታ ኮሚቴ ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
እያንዳንዱ ተወዳዳሪ ( ተጫራች) የመወዳደሪያ ዋጋ ሰነድ ስልጣን ባለው አካል የተፈረመበትና የተሟላ አድራሻውን የሚገልፅ ማህተም ያረፈበት መሆን አለበት፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ በባንክ በ ተረጋገጠ CPO ብር 5,000 ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
የጨረታ መዝጊያ ዕለትና ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፤ ኮ/ ቀ/ ክ/ ከተማ ወረዳ 9 የመሰረተ እድገት
የመጀመርያ ደረጃ ት/ ቤቱ ከጦር ኃይሎች ኮልፌ በሚወሰደው
መንገድ ሀሳንድ ኤንባሲ ከፍ ብሎ ይገኛል፡፡
ስልክ ቁጥር 011 273 82 34/011 280 07 42
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
በኮ/ ቀ/ ክ/ ከተማ ትምህርት ፅ/ ቤት የመሠረተ
ዕድገት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ ቤት
_______________________________
Category : Cleaning and Janitorial., Cleaning and Janitorial Equipments, Education and Training., Books and Education Materials, Electrical and Electronics, Electronics Equipment, Installation and Maintenance, Laboratory and Chemicals, Laboratory Equipments, Medical Equipment and Supplies, Medical/Laboratory Equipment, Office Supplies and Stationery, Office Items and Equipment, Plastic/ Pipes and Fittings, Pipes and Tubes, Printing and Publishing., Printing and Publishing Service, Purchase., Textile and Leather Products, Textiles/ Fabrics and Wearing
Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 6 ቀን 2012
Deadline :2020-03-30 [መጋቢት 21]
back to home