Walia tender audit7

ለውጭ ኦዲት ምክር አገልግሉ
ግዥ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
004/2012
ወላይታ ልማት ማህበር የማህበሩን ዋና ጽ/ቤት እና የቢዝነስ ተቋማቱን ሂሳብ ከቀድሞ GAAP/FASB ወደ አለም አቀፍ የሂሳብ ሪፖርት አቀራረብ ማለትም IFRS/IPSAS ለመተካት እና በተጨማሪ የማማከር አገልግሎትን በውጭ ኦዲተር ባለሙያዎች ለመስራት ስለፈለገ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ አውጥቶ አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር ውል በመግባት ለማሰራት ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ።
በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው
የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የACCA” ተመራቂና አግባብነት ያለው የሥራ ፈቃድና በአዲሱ የሂሳብ ሪፖርት አቀራረብ (IFRS/IPSAS)ልምድ ያለው፣
የተእታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ቢጋር (TOR) የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ ) በመከፈል ከማህበሩ ግዥና ንብረት አስ/ር ክፍል እና በማህበሩ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ገዝተው መውሰድ ይችላሉ።
ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ ለመወዳደር ባቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 1% ማስያዝ አለባቸው።
ተወዳዳሪዎች የሚወዳደሩበትን የተሟላ የቴክኒክና የፋይናንሻል ሰነድ ኦርጂናል እና ኮፒ በሚል ተለይቶ ለእያንዳንዱ ሁለት (2) ኮፒ በታሸገ በተለያየ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በማህበሩ ሥራ ሰዓት ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በማህበሩ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 13 በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ጨረታውን በ15 ኛው የሥራ ቀን በ8 ፡30 ሰዓት ታሽጎ ልክ በ9 ፡00 ሰዓት ይከፈታል ። ቴክኒካል ፕሮፖዛል ተከፍቶ ከተገመገመ በኋላ ያለፉት ተወዳዳሪዎች ፋይናንሻል ፕሮፖዛል ብቻ ይከፈታል። ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፀንቶ ይታያል። ልማት ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ስልክ ቁጥር ፡- 0461801191- የዋና ጽ/ ቤት
0011-572842- የአ/ አበባ
FAX 0465510037
የወላይታ ልማት ማህበር
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 14፥2012
Deadline: May 7, 2020