Walia tender Tips 4

በመወዳደሪያ ሀሳብ መጠየቂያ የሚፈፀም ግዥ
፩. የመወዳደሪያ ሀሳብ መጠየቂያ ከሦስት ላላነሱ እና ከሰባት ላልበለጡ በግዥ ፈፃሚው አካል ለሚመረጡ ዕጩ ተወዳዳሪዎች መላክ ይኖርበታል፡፡ የምክር አገልግሎቱ የሚጠይቀው ወጪ በመመሪያ ከሚወሰነው የገንዘብ መጠን በላይ ከሆነ ዕጩ ተወዳዳሪዎች የሚመርጡት በውድድሩ ተሳታፊ ለመሆን የሚፈልጉ ሀሳባቸውን እንዲገልፁ ከተጠየቀ በኋላ ይሆናል፡፡
፪. የመወዳደሪያ ሀሳብ መጠየቂያ ቢያነስ የሚከተሉትን መረጃዎች መያዝ አለበት፤
ሀ. የግዥ ፈፃሚውን አካል ስምና አድራሻ፣
ለ. የሚፈለገውን አገልግሎት የሚያሳይ የማጣቀሻ ጽሑፍ፤
ሐ. የጥቅም ግጭትን ሊያስከትል የሚችል የምክር አገልግሎት በሚሆንበት ጊዜ በዚህ ዓይነቱ ውድድር የሚቀርቡ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ከምክር አገልግሎቱ በማስከተል ከምክር አገልግሎቱ ጋር በተያያዘ ከሚከናወኑ የዕቃ አቅርቦትና የግንባታ ሥራዎች ራሳቸውን ማግለል የሚገባቸው መሆኑን የሚገልጽ ማሳሰቢያ፤
መ. የመወዳደሪያ ሀሳቦችን መገምገሚያ መስፈርቶችን፣ ለዋጋና ለሌሎች መስፈርቶች የሚሰጡውን ነጥብ፣ መስፈርቶቹ የመወዳደሪያ ሀሳብ በሚገመገምበት ወቅት ጥቅም ላይ የሚውሉበትን አኳኋን፤
ሠ. የመወዳደሪያ ሀሳብ የሚቀርብበትን ቦታና የመጨረሻ ቀን፣
፫. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ሀሳብ ለማዘጋጀት የሚያስችላዠው በቂ ጊዜ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
፬. ግዥ ፈፃሚው አካል አንደኛ ሆኖ ከተመረጠው ዕጩ ተወዳደሪ ጋር በመወዳደሪያ ሀሳቡ ውስጥ የተመለከተውን የአገልግሎቱን ባህሪ፤ መጠን እና አደረጃጀት የሚመለከት ድርድር ማካሄድ ወይም ማሻሻያ እንዲደረግ መፍቀድ ይችላል፡፡
፭. ግዥውን የሚፈጽመው መ/ቤት በአሸናፊነት ሊመርጥ የሚችለው በመወዳደሪያ ሀሳብ መጠየቂያ ሰነድ በተመለከተው የመገምገሚያ ማስፈርት እና ሥርዓት መሠረት በሚካሔደው ግምገማ ያቀረበው የመወዳደሪያ ሀሳብ ይበልጥ ጠቃሚ ሆኖ የተገኘውን ተወዳዳሪ ነው፡፡
©walia tender