Walia tender 9

የተራዘመ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ አገልግሎት የማይሰጡ ልዩ ልዩ የተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች መለዋወጫዎች፣ አገልግሎት የማይሰጡ ቁርጥራጭ እና ሙሉ የማጠናከሪያ ብረቶች (ፌሮዎች) እና እገልግሎት የማይሰጡ የተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች አካል ከፍሎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ በጨረታ ቁጥር መሣ/ተሸ/አሰ/ጥ/ደ/የሥ/ሂ/02/2012 ዓ.ም መጋቢት 13/2010 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ መውጣቱ ይታወሳል ይሁን እንጂ በተቀመጠው ጊዜ ለመፈጸም የኮረና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታትና ለመቆጣጠር ሲባል በተጣለው እገዳ ምክንያት በጨረታ ማስታወቂያው ላይ በተገለጸው ጊዜ መፈጸም ባለመቻሉ ከአሁን በፊት የጨረታ ሰነድ ላልገዛችሁና ገዝታችሁ ላላስገባችሁ ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያ የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን ከዚህ ቀጥሎ በዝርዝር በተቀመጠው መሰረት እንዲፈጸም ይደረጋል፡፡
በመሆኑም:-
ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት በአየር ላይ ይውላል፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 / ሶስት መቶ/ በመከፈል በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት:- ባህርዳር ከተማ ቢሮ ቁጥር 12 (058-222-11-32/15)፤ በጎጃም ገ/መ/ ጥገና ጽ/ቤት:በደ/ማርቆስ ከተማ (058-771-18-18)፤ በሰሜን ሸዋ ገ/መ/ ጥገና ጽ/ቤት፡- በደ/ብርሃን ከተማ (ጠባሴ) (011-681-30-66)፤ በወሎ ገ/መ/ ጥገና ጽ/ቤት በደሴ ከተማ (033-111 -44-23)፣ በጎንደር ገ/መ ጥገና ጽ/ቤት፡- ጎንደር (አዘዞ) ከተማ (058-114-00-67) እንዲሁም በአዲስ አበባ ሳሪስ አካባቢ ነጋ ቦንገር (ዳማ) ሆቴል ጀርባ በሚገኘው የኤጀንሲው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (011-443-13-40) ጨረታው ከወጣበት ከ17/08/2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 03/09/2012 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚገዙበትን የጠቅላላ ዋጋውን 2% በ ባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጋራንቲ ለ60 ቀን ጸንቶ የሚቆይ በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ስም ማስያዝ አለባቸው::
የሚሸጡትን ዕቃዎችና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ::
ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን ዋናውን እና ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ ባህርዳር ከተማ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ17/08/2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 3/9/2012 4 ፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡ ፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 በ3/9/2012 ዓ. ም በ 4 ፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን በ 4:30 ሰዓት ይከፈታል ፡፡
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ከጨረታ ሰነድ ዝግጅት ጋር በተያያዘ ለሚያስፈልግ የበለጠ መረጃ
የሚከተሉትን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
ለመሳ/ ተሽ/ አስ/ ፕ/ ደ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር -12
ስልክ ቁጥር: - +251-058-222-11-32/15
ፖ. ሳ. ቁ: -382 ባርህ ዳር
አማራ ገጠር መንገዶች
ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 17፥2012
Deadline: May 11, 2020