Walia tender 4

Walia tender 4


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2012
የምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2012 ዓ.ም ለሥልጠና አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቋሚ እና አላቂ የሥልጠና እና የቢሮ ዕቃዎችን፣ ማሽኖችን እና መሣሪያዎችን እንዲሁም የአገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ጨረታውን ለመጫረት የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርቶች መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

ተጫራቶች ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉበትን፣ በአቅራቢነት ዝርዝር መመዝገባቸውን እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚገልጹ ማስረጃዎቻቸውን ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ መንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ሕንፃ ኛ ፎቅ ላይ በስራ ሰዓት በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመከፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ዋጋ የሚሰጡት ኮሌጁ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ብቻ ሲሆን በራሳቸው ሰነድ ዋጋ ሞልቶ የሚያቀርብ ተጫራች ድርጅት ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂነቱን ባለቤቱ ይወስዳል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ እና የውል ማስከበሪያ በየሎቱ በተጠየቀው መሠረት በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ ምሥራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጁ ስም አዘጋጅተው ማለትም Addis Ababa City Government TVET Agency Misrak Polytechnic College/ በሚለው ስም ኣሰርተው ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በመፈረም የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተም በየገፁ በማድረግና የሚወዳደሩበትን ዋጋ በተሸጠላቸው ሰነድ ላይ ብቻ በግልፅ በታሸገ ፖስታ ለየብቻው እንደየሎታቸው ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ በፖስታዎቹ ላይ የሚጫረቱባቸውን የጨረታ ዓይነት በመሙላት የአስተዳደር ሕንፃ ኣንደኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፤
በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅታችሁ መሳተፍ የምትፈልጉ ከጥቃቅንና አነስተኛ ጽ/ ቤት በኮሌጁ ስም በቅርብ ጊዜ የተፃፈ ዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች በየንግድ ዘርፋቸው ብቻ መጫረት ይኖርባቸዋል፡፡ ከንግድ ዘርፋቸው ውጪ የሚጫረቱ ድርጅቶች ኮሌጁ አያወዳድርም ለሚጫረቱት እያንዳንዱ ነጠላ ዕቃ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡ ሎት ፣2 እና 3 እንዲሁም በቀላሉ በእጅ ሊመጡ የሚችሉ ዕቃዎችን ተጫራቾች ናሙና ጨረታው ከመዘጋቱ ከሦስት ቀን በፊት ጀምሮ ናሙናውን ጨረታው እስከ ሚዘጋበት ዕለት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ማሽኖችና ትላልቅ ዕቃዎች በቀላሉ መምጣት የማይችሉ ዋጋቸው ከፍተኛ የሆነ ዕቃዎች በፎቶግራፍ በማቅረብና በshop ማሳየት ይጠበቅባችኋል፡፡
በኮሌጁ የሚዘጋጅ ናሙና ሲኖር በግልፅ ቦታ የሚታይ ሲሆን ሌሎች በስፔስፊክሽናቸው መሰረት የሚወዳደሩ ናቸው፡፡
በግምገማ ወቅት እኩል ነጥብ ቢያገኙ በአዋጅ አንቀፅ 1519.26 መሰረት ለአገር ውስጥ ምርት ወይም አገልግሎት ቅድሚያ ይሰጣል፡፡
በብዛት እቃ ላቀረበ ተጫራች የሚሰጥ ይሆናል፡፡
በድጋሚ አከል ቢወጡ በእጣ ደስያሰ፡፡
8. ጨረታው በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታ ቡድን አባላት እና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ በ4 ፡30 ሰዓት የአስተዳደር ሕንፃ ሦስተኛ ፎቅ አዳራሽ ውስጥ የሚከፈት ይሆናል፡፡

9 የጨረታ ዋጋ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከሚከፈትበት ዕለት ጀምሮ 60 ቀን ይሆናል፡፡

10. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ፡- 22 ማዞሪያ ከትራፊክ ጽ/ቤት ወደ እንግሊዝ ኤምባሲ በሚወስደው መንገድ ከአስፋልቱ፡ 500 ሜትር ገባ ብሎ ከአዲስ ኮሌጅ ፊት ለፊት ወይም ከእንግሊዝ ኤምባሲ ወደ 22 ማዞሪያ በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ገባ ብሎ ይገናል፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 0116-18-09-14/0116-18-19-49/0116-18-08-01
በምሥራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ


Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 17፥2012
Deadline: May 4, 2020




back



Report Page