Walia tender 3

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 0002/2012
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የቂሊንጦ ቁ.2 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በ2012 ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዢዎች ለመፈፀም አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
አላቂ የቢሮ እቃዎች
አላቂ የትምህርት እቃዎች
የተለያዩ የፅዳት እቃዎች
የደንብ ልብስ
ቋሚ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፡፡
በዚሁ መሰረት :
በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
በመንግስት እቃ አቅራቢነት የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው
የዘመኑን ግብር የከፈሉ
ተጫራቾች የማይመለስ 100 መቶ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከት/ቤቱ ፋይናንስ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ማህተም ስምና ፊርማቸውን በማኖር ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2 ፡30 እስከ 11 ፡00 ሰዓት ድረስ በት/ቤቱ ፋይናንስ ኦፊሰር ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ብር 3,000 / ሶስት ሺ ብር / ወይም በባንክ የተረጋገጠ /CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በወጣ በ 11 ኛው የስራ ቀን በ 4 ፡ 30 ሰዓት ይከፈታል ::
ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ማረሚያ ፊት ለፊት
ሞባይል 0913082316 /0913581157
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍ ለ ከተማ ቂሊንጦ ቁ 2 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ ቤት
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 17፥2012
Deadline: May 4, 2020