Walia tender 20

Walia tender 20


የጨረታ ማስታወቂያ ብግጨ 33/2012

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2012 የበጀት ዓመት ከመንግስት በተመደበለት በጀት DITCH SIDE CHANNEL CONSTRUCTION AT HEALTH CAMPUS በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ሥራውን መሥራት የሚፈልጉ ተጫራቶች፡

በዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የቲን ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማቅረብ የሚችሉ፣
ለሥራ የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል፣ ማቴሪያልና ማሽነሪዎችን ሙሉ በሙሉ በራሱ አቅርቦ መሥራት የሚችል እና በደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የግንባታ ሥራ ፈቃድ ያላቸው ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፣ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ዋጋ ሞልተው ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00/ አንድ መቶ ሽህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም አሠርተው ማቅረብ ሲኖርባቸው በጥቃቅን የተደራጁ ከአደራጃቸው የመንግስት መ/ቤት የዋስትና ደብዳቤ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም በማሠራት ማቅረብ አለባቸው ፣
አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀለት ከ7/ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ8 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ የሚችል መሆን አለበት፣
ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሥራ ተቋራጮች ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 እና አዲስ አበባ አራት ኪሎ ከቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ወረድ ብሎ ሮሚና ካፌ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮቁጥር 07 ድረስ በመቅረብ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፣
ተወዳዳሪ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላትና በማሸግ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡59 ድረስ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በመቅረብ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
. ጨረታው በ22 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4 ፡30 በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታን ጨምሮ ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
የጨረታውን ፋይናንሽያል ኦርጅናል ዶክመንቶች እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሸገ ፖስታ በማድረግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የመ/ቤቱን ሙሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማህተም በማድረግ በተጠቃለለ አንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ሲኖርባቸው ፋይናንሽያል ዶክመንቶች ከኦርጅናሉ በተጨማሪ አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሣሰቢያ፡የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀናት ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 058-771-66-91 ደብረ ማርቆስ መጠየቅ ይችላሉ::

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ



Posted: አዲስዘመን ሚያዝያ 16፥2012
Deadline: May 15, 2020


back

Report Page