Walia tender 17

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 54/2012
የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለሚገነባቸው ለዋናው ቢሮ ግንባታ፣ ለአማኑኤል፣ ለዳንግላ፣ለቻግኒ የገጠር ሽግግር ማዕከል ግንባታ እና ለሌሎች ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ
አልሙኒየም ትራኪንግ ከነ ስዊቶች (Aluminum Trunket and Accessories (Single, Double, and Triple Switches)
የአቅርቦትና የገጠማ ስራዎች የዳታና የቴሌ ሲስተም (TELE DATA NETWORK SYSTEM)፣
ፋየር አላርም ሲስተም (FIRE ALARM SYSTEM)፣
ሲሲ ቲቪ (CLOSED CIRCUIT TV SYSTEM (P Based CCTV) እና
መብረቅ መከላከያ (LIGHTNING PROTECTION SYSTEM) የአቅርቦትና የገጠማ ስራ ስራዎች ለመግዛት ህጋዊና ብቃት ያላቸውን ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ አማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቀበሌ 11 ኮብል አክሲዮን ማህበር ፊት ለፊት ቢሮ ቁጥር 11 የማይመለስ ብር 200.00 / ሁለት መቶ ብር / በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፡፡ የጨረታው ውድድር በሎት/ በምድብ ድምር ዋጋ የሚታይ ሲሆን በአንድ ሎት/ ምድብ ለተጠየቁ እቃዎች ለሁሉም (ሙሉ በሙሉ) ዋጋ መሞላት እንዳለባችሁ እናሳሰባለን፡፡ ነገር ግን ለድርጅቱ የተሻለ ጥቅም ያስገኛል ተብሎ ከታመነበት በድርጅቱ መመሪያ ገጽ 10 አንቀጽ 14.2.1 ተራ ቁጥር 4 መሰረት ውድድሩን በነጠላ ዋጋ በማወዳደር ዝቅተኛ የሆነውን በመምረጥ ግዥ ሊፈፅም ይችላል፡፡
የጨረታ ሰነዱን አ/አ 4 ኪሎ ፕሬስ ድርጅት ጀርባ በሚገኘው በአ/አ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ መግዛት (መውሰድ) የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን ስለ አአ ጽ/ቤቱ መረጃ ለመጠየቅ ስልክ ቁጥር +251 11265652 0918800364፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ኛው ቀን (16 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር ) ከቀኑ 8 ፡ 00 ሠዓት ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 16 ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8 ፡ 00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከቀኑ 8 ፡30 ሠዓት በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 18 ይከፈታል፡፡
በሚቀርበው የጨረታ ሰነድ ማሟላት ያለበት፡
3.1 በዘርፉ የንግድ ስራ ፈቃድና ለዘመኑ ስለመታደሱ ማረጋገጫ ፣
3.2. ማንኛውም የወቅቱን የመንግስት ግብር ለመክፈሉ ወይም ሌሎች ግዴታዎችን ስለመወጣት ማረጋገጫ ፣
3.3 የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣
3. 4 የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፣ ነገር ግን የሚያስይዘው ማስከበሪያ ከብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) መብለጥ የለበትም፡፡
3.5.ድርጅቱ ከአሸናፊው ድርጅት ንብረቱን ከመረከቡ በፊት ናሙና አስቀርቦ የዕቃዎችን ትክክለኛነት የጥራት ቴስት በማሰራት እና በድርጅቱ አማካሪዎች በማረጋገጥ ትክክለኛነቱን ሲያሟላ ብቻ ይረከባል፡፡ ከህጋዊ ተቋማት ለሚደረግ የጥራት ማረጋገጫ ክፍያ በሻጭ ይሸፈናል፡፡
3.6 በጨረታው ቅር የተሰኘ ተጫራች የጨረታ ውጤቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ብቻ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል፡፡
የጨረታ ውድድሩን አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት እቃዎችን በራሱ ወጪ ፕሮጀክቶቹ በሚገኙበት ከተማ (በየሎቱ /በተናጠል/ በተጠቀሰው ማስረከቢያ ቦታ) ድረስ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ በማቅረብ ያስረክባል፡፡
የጨረታ አሸናፊው ለአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10% የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና /የውል ማስከበሪያ/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያስይዛል፡፡
የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ45 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
የጨረታ ተወዳዳሪዎች በሌሎች ተወዳዳሪዎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችሉም፡፡
በጨረታ ሠነዱ በእያንዳንዱ ገጽ እና ፖስታው ላይ ፊርማና የድርጅቱ ማህተም ሊኖር ይገባል፡፡
ድርጅቱ የጨረታ አሸናፊ ከሆነው አቅራቢ የጨረታውን ይዘት ሳይቀይር ከገዛው ዕቃ መጠን ላይ በየሎቱ ጠቅላላ እቃ አይነትናመጠን ወይም በእያንዳንዱ የእቃ አይነትና መጠን ለገዥ ጠቃሚነው ብሎ ከታመነ ውል ሲይዝ 50% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡ከውለታ በኋላ 50% ሊጨምር ይችላል፡፡
ከጨረታ ሳጥን መዝጊያ ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ውለታ ወስዶ ናሙና ለአማካሪ በማቅረብ ሲፀድቅለት ብቻ ያቀርባል ገጠማ የተጠየቀባቸውን እቃዎች አቅርቦ ይገጥማል፡፡
ውድድሩ በሎት ድምር አሸናፊ የሚል ቢሆንም ገዥ ድርጅቱን የሚጠቅም ሆኖ ከተገኘ በነጠላ ዋጋ በማወዳደር አሸናፊ ሊመርጥ ይችላል፡፡
ከድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ፡- ስልክ ቁጥር፡- 058-218-0711 - ፋክስ 0582 180538/0583204001 ሞባይል ቁጥር፡- 09-18-71-6616 /0913454110/09-12-78-3066
የአማራ የህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት
Posted:አዲስዘመን ሚያዝያ 16፥2012
Deadline: May 9, 2020