Walia tender 14

Walia tender 14


የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር አ/ አ/ ከ/ ፍ/ ቤት/02/2012

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤

ሎት1- የፎቶ ኮፒና የፕሪንተር ቀለሞች
ሎት2 -- የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች
ሎት.3 - የአልሙኒየም የሻተር እና የጨርቅ መጋረጃ ስራዎች
ሎት 4 --የኮምፒውተር ፣ፕሪንተርና የፎቶ ኮፒ እና ፋክስ ማሽን ጥገና ስራዎች
ሎት-5- የተለያዩ የቢሮ ጥገናና ዕድሳት ስራዎች የቢሮ ዕቃዎች የጥገና ስራ
1- የግዥ መለያ ቁጥር አ/አ/ከ/ይ/ሰ/ፍ/ቤት/02/2012

2. ግዥው ግልጽ ጨረታ ነው

3. ጨረታ ሰነድ የወጣበት ወር ሚያዚያ 2012 ዓ/ም

ተጫራቾች ህጋዊ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ! የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ፤ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆኑ ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የዋስትና ደብዳቤ የሚያቀርቡ ለሎት 4 እና 5 ለቀረቡት የእጅ ዋጋ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ሆነው ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ሥራ ሰርተው የድጋፍ ደብዳቤ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው እና ላሸነፉበት እቃ የውል ማሰከበሪ ማስያዝ የሚችሉ እንዲሁም ቋሚ የስራቦታ ወይንም ድርጅት ያላቸው ሆነው በቅድመ ምልከታ ወቅት ድርጅታቸውን ወይንም የሥራ ቦታቸውን ማሳየት ፍቃደኛ የሆኑ ከዚህ በፊት በፍርድ ቤቱጨረታ አሸንፈው በገቡት ውል መሰረትግዴታቸውን የተወጡ።

ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 ( ሃምሳ ብር ) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ከግዥ ፈጻሚ የአዲስ አበባ ከተማ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 17 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ ለተገለፁት ዕቃዎች ለተወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
ሎት 1 ብር 500 ብር
ሎት2- 500 ብር
ሎት 3 -1000 ብር
ሎት 4-500 ብር
ሎት-5- 500 ብር ወይም ተጫራቾች በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ያደራጃቸው መስሪያ ቤት ለዋስትናው በፍርድ ቤቱ አድራሻ የተጻፈ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው::
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ኦርጅናል እና ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ በየሎቱ በግልጽ ኢንቨሎፕ ላይ በመፃፍ እና የድርጅቱ ማኅተም እና ፊርማ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ 11 ኛው ቀን በ 4 ፡ 00 ሰአት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚያው እለት 4 ፡ 30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
ተጫራቾች ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ ከ 1 ቀን በፊት ለሚጫረቱበት በሰነዱ ላይ ናሙና እንዲቀርብ ለተጠየቀባቸው እቃዎች በጨረታው ለመወዳደር ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ተጫራቶች በጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩት ዕቃዎች የእያንዳንዱን ነጠላ ዋጋ እና ድምር ዋጋ VAT ጭምሮ ማካተት ይኖርባቸዋል። ፍርድ ቤቱ ጨረታውን ለመገምገም የሚጠቀምባቸው መስፈርቶች ዕቃዎቹ ፍርድ ቤቱ ባስቀመጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት ወይም በሚቀርበው ናሙና ጥራት፤ ዋስትና፤ አነስተኛ ዋጋ እና አጠቃሎ የማቅረብጊዜ ግምት ውስጥ ይገባል።
ፍርድ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
በየሎቱ የሚሳተፉ ተወዳዳሪ ድርጅቶች በዘርፉ የሚሰሩ ድርጅቶች ብቻ መሆን አለባቸው።
ኮፒ እና ኦሪጅናል ኢንቨሎፕ በተናጠል (ለየብቻ) በፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
አድራሻ

ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሜክሲኮ ፍሊፕስ ህንጻ አጠገብ

የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ህንጻ

1 ኛ ፎቅ ላይ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 17

ስልክ ቁጥር 0118-69-78-28/011-515-70-40

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት


Posted: አዲስዘመን ሚያዝያ 16፥2012
Deadline: May 4, 2020


back

Report Page