Walia tender 12

Walia tender 12


የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለተከታታይ ሶስት ዓመታት ኦክስጂን የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የኦክስጂን ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ከፌዴራል ሀገር ውስጥ ገቢ ወይንም ከሌሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግስት መ/ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በመንግስት ጨረታዎች መካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ፣ በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመረጃ መረብ ድረ-ገጽ /web-site/ ላይ የተመዘገቡ፣ የሙያ ፈቃድ እና የሚጫረቱበት ዋጋ ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ የሚበልጥ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ጨረታ የጨረታውን ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ብር 35,000.00 ( ሰላሳ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO የጨረታው ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 50.00 ( ሃምሳ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሠነድ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ብቻ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 04 ቀን 2012 ዓ. ም ከቀኑ 8 ፡30 ሰዓት ድረስ በሆስፒታሉ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡ ፡
ጨረታው ግንቦት 04 ቀን 2012 ዓ. ም ከቀኑ 8 ፡40 ሰዓት ላይ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን

ስልክ ቁጥር፡-251-468-20-96-17 ፋክስ 251-462-20-87-55

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል



Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 17፥2012

Deadline: May 12, 2020



back


Report Page