Walia tender 12

የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር- ገሚ/02/ ፅ/ ዳ/2012
የገቢዎች ሚኒስቴር በ2012 በጀት ዓመት ለሁለተኛ ጊዜ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን የፅዳት እቃዎች እና ተዛማጅ መሳሪያዎች ግዥን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ::
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ።
ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ።
በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት።
ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዥ የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ ብር በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ወይም ከሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመሰስ ብር አንድ መቶ (100.00) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ መገናኛ አካባቢ ከሚገኘው የሚኒስቴሩ ዋና መስሪያ ቤት የግዥ ቡድን ህንፃ ቢሮ ቁጥር 301 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ::
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከግንቦት 6 ቀን 2012 ዓ . ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።ጨረታውም በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4 ፡ 30 ሰዓት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
የጨረታው አሸናፊ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 10% (አስር በመቶ) ከባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ በማስያዝ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 0116-673845
የገቢዎች ሚኒስቴር
posted date:አዲስዘመን ሚያዝያ 15፥2012
deadline:May 14/2020