Walia tender 11

የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት(አኢግልድ) የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች (Office Furniture) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣በመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዝርዝር የተመዘገበበት የምስክር ወረቀትና ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ እንዲሳተፍ የተፃፈለትን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡ ለዚህ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ ዢ፣ ንብረት አስተዳደር እናጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቶች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዳቸው በተለያዩ በሰም በታሸገ ፖስታዎች በማድረግ እንዲያቀርቡ እያሳሰብን ፤ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በማግስቱ በ16 ኛው ቀን በ4 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4 ፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢኢግልድ ዋና መ/ ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 ( ሠላሳ ሺ ብር) በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (Ethiopian Industrial Inputs Development Enterprise) ስምበሲ.ፒ.ኦ. ከቴክኒካል ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ አዲስ አበባ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ አካባቢ በስተ ሰሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ ወደ ዮሃንስ በሚወስደው መንገድ ጣሊያን ሰፈር (የቀድሞ ጅንአድ መ/ቤት)፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ ፦ በስልክ ቁጥር 01-13-69-20 36 /0113-69-1995 በመደወል ወይም
www.mewit.com.et or www.eiide.com.et ማግኘት ይችላሉ
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 17፥2012
Deadline: May 10, 2020