Walia tender 10

የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር :-
ሰ/ ማስ/ ማዕከል DPKC/OTO2/2012B
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰላም ማስከበር ማዕከል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም ለተጨማሪ ዕሴት ታክስ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣ የአቅራቢነት የድህረ-ገፅ ምዝገባ የምስክር ወቀረት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የቲን ሰርተፍኬት ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው የሚከናወነው በግልፅ ጨረታ ስነ-ስርዓት እና ይህንኑ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ባወጣው የመንግስት የግዥ አዋጅ መሰረት ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው::
ከላይ በመግለጫ ለተጠቀሱት የጨረታ ሰነዶች ለእያንዳንዳቸው ፍላጐት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዶችን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 በተገለፀው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የጨረታው ሰነድ የሚቀርበው በአካል ቢሮ ድረስ በመምጣት ሲሆን ከዚህ በላይ በዝርዝር ከተጠቀሰው የጊዜ ሰሌዳ ዉጭ ዘግይቶ ለሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ኃላፊነት የማንወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ተጫራቾች በሀርድ ኮፒ በወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ያልተካተቱ የተለያዩ የጨረታ መመሪያዎች ስላሉ ማንኛውም ተጫራች በሶፍት ኮፒ ለመውሰድ ባዶ ሲዲ ብቻ ይዞ መምጣት ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ከጨረታ መክፈቻ አንድ ቀን ቀድሞ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚመጣ ናሙና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
መስሪያ ቤታችን እንደ አስፈላጊነቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ እና የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ የሚያገለግል አድራሻ
* ከሚኒሊክ ሆስፒታል ወደ ጃንሜዳ በሚወስደው መንገድ መከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል
- ስልክ ቁጥር 011-1-54-01-50
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር
የሰላም ማስከበር ማዕከል ግዥ ቡድን
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 17፥2012
Deadline: May 9, 2020