Walia tender 10

ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር AA-PP-01/2012
የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት፡-1 የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች
ሎት፡- 2 የጽዳት እቃዎች
ሎት፡- 3 የመኪና ዲኮር እቃዎች
ሎት፡-4 ቋሚ እቃ ግዥ
ሎት፡- 5 የተዘጋጁ የደንብ ልብሶች እና ጫማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
1.1 የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
1.2 የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው
1.3 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
1.4 የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና ሰርተፍኬት ያላቸው
1.5 በግዥ ኤጀንሲ አቅራቢዎች ሊስት የተመዘገቡ እና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
1.6 ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ስለ ግብር አከፋፈል የሚገልጽ
በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 ብር በመክፈል ሃያ ሁለት ጎላጎል ታወር ፊት ለፊት ትራፊክ ፖሊስ ህንፃ በሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት ሰባተኛ ፎቅ ሂሳብ ክፍል በግንባር በመቅረብ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት 5,000.00 / አምስት ሺህ ብር/ ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በድርጅቱ ስም ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከሲፒኦ ውጪ የሚቀርብ ማስያዣ ከጨረታ ውጪ ያስደርጋል፡፡ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው እንደተረጋገጠ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
ተፈላጊውን የጥራት ደረጃ ያልጠበቀ እቃ ማቅረብ ከአቅራቢነት ያሰርዛል፡፡
ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሎት በመለየት ዋጋቸውን ጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘጋጀው የዋጋ መሙያ ላይ ብቻ ያንዱን ዋጋ፤ ጠቅላላ ዋጋ እና ቫትን አካቶ ያለውን ድምር በመጨመር ጠቅላላ ዋጋ በመሙላት እና ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች በሙሉ ጨረታው ከመከፈቱ ከ3 ቀናት በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
ከጨረታ ሰነዱ ውጪ ተሞልቶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም
ጨረታው በ 11 ኛው ቀን 4 ፡ 00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4 ፡ 30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ 3ኛ ፎቅ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
የጨረታ ሂደቱን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከውድድር ውጪ ይሆናሉ፡፡
መ/ቤቱ ጨረታው በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- +251 118 93 16 69/ +251 11 8 93 22 75 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የብልጽግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት
Posted date:አዲስዘመንሚያዝያ 16፥2012
Deadline:May 5/2020