Walia tender 1

የጨረታ ማስታወቂያ 02
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ከዚህ በታች በሎት የተከፋፈሉትን ግዥዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
ሎት 1፡- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ኮምፒዩተር፣ፕሪንተር ላፕቶፕ አና ፎቶ ኮፒ ማሽን
ሎት 2፡- የፈርኒቸር ዕቃዎች
ሎት 3፡- የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ግማሽ ሊትር ውሃ፣ ቆሎና የተፈጨ ቡና እና የፆምና የፍስክ ምግቦች በሰነዱ ላይ በተዘረዘረው መሰረት
ሎት 4 ፡- የዕቃ መጫኛ አይሱዙ አና ደረጃ 1 አገር አቋራጭ አውቶቡስ እና በከተማ ዙሪያ አውቶቡስ ኪራይ
ሎት 5፡- የጽዳት ዕቃዎች
ሎት 6፡- ለቀላል ተሽከርካሪ ሰርቪስና ጥገና የሚያደርግ ጋራዥ
ሎት 7፡- ብልሽት ሲያጋጥም ተሽከርካሪን በከሪን አንስቶ ወደ ጋራዥ የሚወስድ የክሪን አገልግሎት በክፍለ ሀገር በኪ.ሜ/ሲፒኦ አያስፈልግም/
ሎት 8፡-የጽህፈት ዕቃዎች
ሎት 9፡- የህትመት ስራዎች
ሎት 10፡- በተለያዩ ጊዜ ሞንታርቦ ፣ጀነሬተር ኪራይ እና አዳራሽ ሙሉ ዲኮር
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቶች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ፣የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የቫት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና አግባብነት ያለው የአቅራቢዎች የምዝገባ የምስክር ወረቀት፡፡
ተጫራቾች ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ቀደም ብለው ናሙና የሚያስፈልጋቸውን ዕቃዎች ናሙናውን ለዕቃ ግምጃ ቤት ማስረከብ አለባቸው። ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ በጨረታው ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይመለስልን ማትሉት ብር 100.00/ አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1 ብር 20,000.00/ ሃያ ሺ ብር/ ፣ ሎት2 ብር 1,000.00/ አንድ ሺ ብር/ ሎት 3 ብር 1,000.00 / አንድ ሺ ብር ሎት 5 ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/ ሎት 6 ብር 1,000.00/ አንድ ሺ ብር/ ሎት 8 ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/ ሎት 9 ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲያሰሩ ADDIs KETEMA suBCITY ADMINISTRATON CHIEF EECUTIVE PURCHASING ADMINISTARATION SUPPORTIVE PROCESS OFFICE በሚል ስም በማዘጋጀት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስገባት ይኖርባቸዋል
ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ /ማሻሻያ/ ማድረግ እንዲሁም እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሰውን ማስረጃዎች አሟልተው በሰም በታሸገ እንድኮ/ ኦሪጂናል እና አንድ/ኮፒ የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን መድዓኒአለም ከግም ሆስፒታል ከፍ ብሎ ባለው አስተዳደሩ ጽ/ቤት 7ኛፎቅ ቢሮ ቁጥር 702 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ እንደተገለጸ የውል ማስከበሪያ 10% /ሲፒኦ/ ዋስትና በማስያዝ ውለታ መግባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ኛው ቀን ከቀኑ 11 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀናት ካልሆነ በ11 ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-0118 69 38 76 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ
አድራሻ፡- መድዓኒአለም ከራስ ሃይሉ መዝናኛ ማዕከል አጠገብ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ህንፃ ዋና ስራ አስፈፃሚ ግዥ ቡድን 7 ኛ ፎቅ በግራ ክንፍ በኩል
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ ቤት ግዥ ቡድን
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 17፥2012
Deadline: May 4, 2020