Walia tender

Walia tender



ዓለም አቀፍ የግዥ ዘዴ


፵፱. ዓለም ዓቀፍ የግዥ ጨረታ
፩. ዓለም ዓቀፍ ግልፅ የጨረታ ዘዴ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችለው የውጭ ኩባንያዎች በጨረታው ተሳታፊ እንዲሆኑ ካለተደረገ በግልፅ ጨረታው ውጤታማ የሆነ ውድድር ሊኖር እንደማይችል የታመነበት እና ግዥው ሚኒስትሩ በሚያወጣው መመሪያ ከተመለከተው የገንዘብ መጠን በላይ ሊሆን ነው፡፡
፪. ዓለም ዓቀፍ ግልፅ ጨረታ በምዕራፍ ፭ የተጠቀሱትን እንዲሁም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሥርዓቶች መከተል አለበት፡፡
ሀ. የጨረታ ማስታወቂያ እና የጨረታ ሰነዶች የዓለም ዓቀፍ ንግድ መገልገያ በሆነ ቋንቋ መዘጋጀት አለባቸው፡፡
ለ. የጨረታ ማስታወቂያ በተዘጋጀበት ቋንቋ በሚታተም፣ በቂ ሥርጭት ባለው እና ዓለም ዓቀፍ ውድድርን በሚጋብዝ ጋዜጣ ላይ የጨረታ ማስታወቂያው መታተም አለበት፡፡
ሐ. የጨረታ ሰነድ የማቅረቢያ ጊዜው የጨረታው ማስታወቂያ ለዕጩ ተወዳዳሪዎች እንዲደርስ ለማድረግ እና ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳባቸውን አዘጋጅትው ለማቅረበ የሚያስፈልጋቸውን በቂ ጊዜ የሚፈቅድ መሆን አለበት፡፡
መ. የዕቃና የአገልግሎት ዝርዝር ከአገር ውስጥ ደረጃዎች ጋር የሚጣጣም ሆኖ በዓለም ዓቀፍ ደረጃዎች ወይም በዓለም ዓቀፍ ንግድ በስፋት የሚሰራበትን ደረጃ መሠረት ያደረገ መሆን አለበት፡፡
ሠ. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የመጫረቻ ዋጋቸውን እንዲሁም የሚያቀርቡትን ማናቸውንም የዋስትና ሰነድ በኢትዮጵያ ብር ወይም በጨረታ ሰነድ በተመለተው እና በዓለም ዓቀፍ ንግድ በስፋት በሚሰራበት የገንዘብ ዓይነት እንዲያቀርቡ መፈቀድ አለበት፡፡
ረ. አጠቃላይ እና ልዩ የውል ቃሎችና ሁኔታዎች በዓለም ዓቀፍ ንግድ የሚሰራባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡


©walia tender

Report Page