TWalia tender
አርጂ ገበያ (ጨረታ ማስታወቂያዎች)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ss NT-T195
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ለሚገኙ ማንኛውንም ኮንትራክተሮች እና አነስተኛና ጥቃቅን የድርጅት ተቋራጮች በንግድ ቢሮ ሚኒስትር የተረጋገጠ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እንዲሁም ከታች የተዘረዘሩትን ስራዎችን እና መስፈርቶች የሚያሟሉ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል:: ፕሮጀክቱ የሚከተሉትን ሥራዎችን ያካትታል፡፡
- Electrical and Sanitary works
- Metal and welding works
- Civil works (including masonry works, carpentry works, painting...)
- Steam and laundry system maintenance work
- Machine erection works
- Installation of air condition unit and repair
- Installation of ventilation system and duct works
- Other related works
ስለሆነም በሙያው ዘርፍ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የምዝገባ ወረቀት ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ተጫራቾች፡ እንዲሁም ብር አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ 1,500,000 እና ከዚያ በላይ በሆነ ዋጋ ቢያንስ ሦስት (3) ፕሮጀክቶችን በተሳካ ሁኔታ ያጠናቀቁና በሙያው ቢያንስ ሶስት (3) ዓመት የሥራ ልምድ ያላቸው፤ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚያወጡት ጨረታ ውስጥ ለመሳተፍ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተሰጠ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር አንድ መቶ ብር / ሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T 195 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በሰም በታሸገ ፖስታ ቴክኒካል ሰነዳቸውን ዋናው እና ቅጂውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ሚያዝያ 7 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት የሠራተኛች የመመገቢያ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን በ9:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ:- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
በስልክ ቁጥር 011 517 4028 /4258 P.O Box 1755
ኢ.ሜይል፡ WoldeM@ethiopianairlines.com / TsegenetF@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
Ethiopian
Categories Construction and Water Works Electrical, Electromechanical and Electronics Mechanical Metal and Metal Working Sanitary and Ceramics
Posted date:አዲስ ዘመን መጋቢት 9 ቀን 2012
Dead line: April 14, 2020[መጋቢት 7]
______________________________