Walia elec sale hawasa1

Walia elec sale hawasa1


የዕቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የደ/ብብ/ህ/ክ መንግሥት የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለተሰማሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ያላቸው፣
የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የተቀበሉትን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ) ብር በመክፈል ከቢሮአችን ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ።
ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 5,000 ( አምስት ሺ ብር) በቢሮአችን ስም በተዘጋጀና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ቢድ ቦንድ ከሰነዱ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
ተጫራቾች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን አላስፈላጊውን መረጃ በማያያዝ ኦሪጅናሉንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ፖስታ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቢሮአችን ለዚሁ ተግባር ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
ጨረታው በ16 ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 8 ፡30 ሰዓት በቢሮአችን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ የጨረታው ማስከበሪያ ገንዘብ ላላሸነፉት ድርጅቶች ወዲያውኑ ይመለሳል፡፡
የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት አሸናፊነቱ በጽሑፍ እንደተገለጸለት ወደ ቢሮአችን መጥቶ አስፈላጊውን የጨረታ ውል መፈረም አለበት፡፡ ይህን ባይፈጽም ቀደም ሲል ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
በክልሉ ግዥ አዋጅና መመሪያ ውስጥ ለአገር ውስጥ ልዩ አስተያየት የሚደረግላቸው አካላት በሚያቀርቡት ማስረጃ መሠረት ይስተናገዳሉ።
ቢሮአችን ጨረታውን አስመልክቶ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 046-221-3134

የደ/ ብ/ ብ/ ህ/ ክ/ መንግሥት የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ሀዋሳ



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 16 ቀን 2012
Deadline: June 7, 2020


© walia tender

Report Page