Walia 11

Walia 11



የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር A.K.K.K.P.D.,/NCB002/2012 ዓ/ ም

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በ2012 በጀት ዓመት ለመምሪያው የስራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ጨረታዎችን በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ሲሆን፣

ስለዚህ፡- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡

በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን እና በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው ይመልከቱ የሚል ፅሁፍ በግልጽ ማቅረብ አለባቸው፡፡
የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፡፡
ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ እና የታደሠ ንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ::
የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ማቅረብ ኣለበት :
አማራጭ ዋጋ እና አማራጭ ዕቃ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም፡፡
በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
በጨረታ ውጤቱ አሸናፊ መሆኖ ከታወቀ የገንዘብ መጠን 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና ለአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ | መምሪያ ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችንና የዋጋ ማቅረቢያዎችን ዘፋይናንሻል/ሰነዶች በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለባቸው፡፡
ማንኛውንም ተጫራቾች የሚያስገባው ሰነድ ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር የሚጫረትበትን ዕቃ አይነት በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታውና በገዙት ሙሉ የጨረታ ሰነድ ላይ ፈርመውና ማህተም በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን ፣ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያሲዙት ሲፒኢ ከቴክኒክ ሰነዶችጋር በአንድ ላይ ታሽገው መቅረብ አለባቸው።
በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን ወይም አገልግሎቱን በራሳቸው ትራንስፖርት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ግምጃ ቤት ወይም በክፍል 6 በፍላጎት መግለጫው በተጠቀሰው የማስረከቢያ ቦታ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው፣
በጨረታ ሰነድ በክፍል 6 ውስጥ በሚገኘው የፍላጎት መግለጫ ላይ በሚገለፀው መሰረት ጨረታ ሰነዱ ላይ በቀረበው መሰረት ናሙና ማቅረብ አለበት ::
ተጫራቾች ያቀረቡት ናሙናም ሆነ አሸናፊ መሆናቸው ሲረጋገጥ የሚያቀርቡአቸው ዕቃዎች ፖሊስ መምሪያው ባወጣውፍላጎት ሙግለጫ /sepecification/ መሰረት መሆኑን በመምሪያው የጥራት ኮሚቴ ወይም በኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ኤጀንሲ አማካኝነት የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡
ናሙናው ገቢ መሆን ያለበት ጨረታው ከሚከፈትበት ከአንድ ቀን በፊት መሆን አለበት፡፡
ተጫራቾች ጎጃም በረንዳ አስፋው ወሰን ሆቴል ጎን በሚገኘው መ/ቤት 5ኛ ፎቅ ግዢ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ቀርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፣
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በማግስቱ በሀኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ በመምሪያው ፋይናንስና ግዢ 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡
በጨረታ ሰነዱ ክፍል 2 ላይ በሚጠቀሰው ቀን 4/9 /2012 ዓ/ ም ጠዋት 4 ፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4:30 ሰዓት ሲሆን በመ/ቤቱ 5ኛ ፎቅ ትንሹ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፣
የጨረታው መከፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሲሆን ይከፈታል፡፡
ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
ለበለጠ መረጃ በስ/ ቁጥር፡- 0112-73-37-35 / 0118 69 61-35 /0112-73-34-04

የአዲስ ከተማ ክፍስ ከተማ ፖሊስ መምሪያ


posted date:አዲስዘመን ሚያዝያ 16፥2012
Deadline:


back

Report Page