Vicle used et medhin 17

Vicle used et medhin 17


የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሣ ከፍሎ ያስቀራቸውን ጋቢናዎች በተናጥል በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ጋቢናዎቹ ቃሊቲ ክራውን ሆቴል በስተጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል በመገኘት ከግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሰኔ 01 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ በመመልከትና የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ። የማስያዣ ዋጋው የጨረታ መነሻው 20 በመቶ ሲሆን ዝቅተኛ የጋቢና የማስያዣ ዋጋ ብር 1000 ነው::

ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት በመሙላት የጨረታውን ሠነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ሰኔ 01 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ቃሊቲ በሚገኘው በማዕከሉ ግቢ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ሰኔ 02 ቀን 2012 ዓ. ም. ከጠዋቱ 3 ፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቃሊቲ በሚገኘው በሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል ይከፈታል፡ ፡ በጨረታው ተሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ከሁለት የሥራ ቀናት በኋላ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን፤ ለአሸናፊዎች ግን ሂሣቡ በገዙት ንብረት ላይ የሚታሰብ ሆኖ፤ የገዙትን ንብረት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የገዙትን ዋጋ አጠናቀው በ10 ቀናት ጊዜ ውሰጥ ንብረቱን ባይረከቡ ለጨረታ ተሳትፎ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልክ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ ክፍያ ፈፅመው ንብረቶቹን በተገለፀው ጊዜ የማያነሱ ተጫራቾች የጥበቃ ወጪ በቀን ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ይከፍላሉ። የጨረታው አሸናፊ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ከከፈለ በኋላ ንብረቱን በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ካላነሰ ከክፍያው ላይ የቅጣት ተቀንሶ ቀሪ ሂሳብ ካለው ተመላሽ ይደረግለታል። ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ያሸነፈውን ጋቢና በአለበት ሁኔታ በአንድ ጊዜ ማንሳት አለበት። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011439-25-89 እና 011439-25-45 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 11 ቀን 2012
Deadline: June 9, 2020


© walia tender

Report Page