Vic sale other 47 debub welo

Vic sale other 47 debub welo


ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ወሎ ዞን ገ/ኢ/ትብብር መምሪያ ለራሱና አገልግሎት ለሚሰጣቸው የዞን መምሪያዎችና ተጠሪ ጽ/ቤቶች በ2012 ዓ.ም

ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
ሎት 2 ለደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ አገልግሎት የሚውል ጀኔሬተር፣
ሎት 3 የመኪና ጎማዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡

በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin number) ያላቸው፡፡
የግዥ መጠኑ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቶች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች ኦሪጂናል ዕቃ መሙላት እና ያሸነፉባቸውን እቃ በባለሙያ ማስፈተሽ አለባቸው፡፡
የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ሲሞሉ ከእያንዳንዱ የዕቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 30 ( ሰላሳ ብር) በመክፈል ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር የእቃውን ጠቅለላ ዋጋ 1.5% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ ሲያሲዙ በመምሪያው የገቢ ደረሰኝ ቆርጦ ኮፒውን ከኦሪጂናል ሰነዱ ጋር መታሸገ አለበት፡፡
አሸናፊው አካል የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የሚያሲዝ ይሆናል፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደቡብ ወሎ ዞን ገ/ኢ/ት/መምሪያ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ውድድሩ በጥቅል (በሎት) ድምር ነው፡፡
ጨረታው ተጫራቶች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4 ፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 033 111 61 34 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 033 111 81 18/19 እና 033 111 81 18 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
መቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- አሸናፊው ድርጅት ( ተጫራች) ኦርጂናል ዕቃ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዕቃውን በየፑሉ በሚገኘው ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን ገ/ ኢ / ትብብር መመሪያ



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 10 ቀን 2012
Deadline: June 3, 2020


© walia tender

Report Page