Vic sale 2

የመኪና ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ዲላ አለልቱ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩኒየን ከዚሁ በታች የተዘረዘሩትን ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሽጥ ይፈልጋል::

የተሽከርካሪዎች ሁኔታ ማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች አ/አ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ገላን የኦሮሚያ የግብርና ሕብረት ሥራ ፌዴሬሽን ገላን የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ በመገኘት ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ማየት ይችላሉ::
የዋናው መኪናና የተሳቢው መኪና መነሻ ዋጋ ከ 2,500,000 የኢትዮጵያ ብር አንስቶ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 20 ፐርሰንት በባንክ በተረጋገጠ የ ክፍያ ሰነድ ሲፒኦ በማቅረብ በማሰያዝ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
የጨረታው አሸናፊ ቀሪውን ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ ማካፈል፡፡ ባይካፈል ግን ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስለትም፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቶች ግን ያስያዙት ገንዘብ ወይም የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል::
መያዣ ሰጪዎች ወይም ተወዳዳሪዎች በጨረታው ቀንና ሰዓት በቦታው ላይ መገኘት ይችላሉ፡፡ ግን ባይገኙ ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
ተሽከርካሪዎቹ በግዥ ስም እንዲዞር ድርጅቱ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡ የስም ማዛወሪያ ወጪን ገዥው ይከፍላል፡፡
ጨረታው ተጫራቾች በአካልም ሆነ ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበ ት በ17/9/2012 ዓ. ም ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4 ፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ሰዓት በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ላይ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ 4 ፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋውን ስርዝ ድልዝ በማይኖረው ተሞልቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ከ 01/9/2012 እስከ 14/9/2012 ዓ.ም የሥራ ቀናት ውስጥ የሚይመለስ 100.00 የኢትዮጵያ ብር በመክፈ ል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ገላን የኦሮሚያ ግብርና ሕብረት ሥራ ፌዴሬሽን ፋብሪካ ማዕከል ጽ/ቤት በማቅረብ ማግዛት ወይም መመዝገብ ትችላላችሁ::
ለበለጠ መረጃ ዲላ አለልቱ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩኒየን በቀጥታ ስልክ ቁ ጥር 0917298265/0577740600 ላይ ደ ወለው መጠየቅ ይችላሉ::
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በም/ መስጋ ዞን በነጆ ወረዳ
የዲላ አለልቱ ኃላፊነቱ የተወሰነ ሁለገብ የገ/ ሕ/ ሥ/ ዩኒየን
Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 01 ቀን 2012
Deadline: May 25, 2020
© walia tender